የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 6:60-64

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 6:60-64 አማ2000

ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ብዙ​ዎቹ ይህን ሰም​ተው፥ “ይህ ነገር የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ነው፤ ማንስ ሊሰ​ማው ይች​ላል?” አሉ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ስለ​ዚህ ነገር እንደ አን​ጐ​ራ​ጐሩ በልቡ ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ያሰ​ና​ክ​ላ​ች​ኋ​ልን? እን​ግ​ዲህ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበ​ረ​በት ሲያ​ርግ ብታ​ዩት እን​ዴት ይሆን? ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ መን​ፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አን​ዳች አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ ይህም እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ቃል መን​ፈስ ነው፤ ሕይ​ወ​ትም ነው። ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ውስጥ የማ​ያ​ምኑ አሉ፤” ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከጥ​ንት ጀምሮ የማ​ያ​ም​ኑ​በት እነ​ማን እንደ ሆኑ፥ የሚ​ያ​ሲ​ዘ​ውም ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበ​ርና።