ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 50

50
ስለ ባቢ​ሎን ውድ​ቀት
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በባ​ቢ​ሎን ላይ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው። 2“ለአ​ሕ​ዛብ ተና​ገሩ፤ አው​ሩም፤ ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ፥#“ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ብቻ። አት​ደ​ብቁ፦ ባቢ​ሎን ተያ​ዘች፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ተላ​ልፎ ተሰጠ” ይላል። ቤል አፈረ፤ ሜሮ​ዳክ ፈራች፤ ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ፤#“ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በሉ። 3ሕዝቤ ከሰ​ሜን በእ​ር​ስዋ ላይ ወጥ​ት​ዋል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባድማ ያደ​ር​ጋል፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም አይ​ገ​ኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ሸሽ​ተው ሄደ​ዋል።
4“በዚ​ያም ወራት በዚ​ያም ጊዜ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የይ​ሁዳ ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ሆነው ይመ​ጣሉ፤ እያ​ለ​ቀ​ሱም መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ይሄ​ዳሉ፥ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ል​ጋሉ። 5ወደ ጽዮን የሚ​ሄ​ዱ​በ​ትን ጎዳና ይመ​ረ​ም​ራሉ፤ ፊታ​ቸ​ው​ንም ወደ ሀገ​ራ​ቸው ይመ​ል​ሳሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል​ኪ​ዳን አይ​ረ​ሳ​ምና መጥ​ተው ወደ ፈጣ​ሪ​ያ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይማ​ጠ​ናሉ።
6“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነ​ዋል፤ እረ​ኞ​ቻ​ቸው አሳ​ቱ​አ​ቸው፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ የተ​ቅ​በ​ዘ​በዙ አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ከተ​ራራ ወደ ኮረ​ብታ ዐለፉ፤ በረ​ታ​ቸ​ው​ንም ረሱ። 7ያገ​ኙ​አ​ቸው ሁሉ በሉ​አ​ቸው፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፦ በጽ​ድቅ ማደ​ሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ተስፋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ስለ ሠሩ እኛ አና​ሳ​ር​ፋ​ቸ​ውም አሉ። 8ከባ​ቢ​ሎን መካ​ከል ሽሹ፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ውጡ፤ በበ​ጎ​ችም ፊት እንደ እባ​ቦች#ዕብ. “አውራ ፍየ​ሎች” ይላል። ሁኑ። 9እነሆ ከሰ​ሜን ምድር የታ​ላ​ላቅ አሕ​ዛ​ብን ጉባኤ አነ​ሣ​ለሁ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ይሰ​ለ​ፋሉ፤ ከዚ​ያም ትወ​ሰ​ዳ​ለች፤ ፍላ​ጾ​ቻ​ቸ​ውም ባዶ​ውን እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ እንደ ብልህ ተዋጊ ፍላጻ ናቸው። 10የከ​ላ​ው​ዴ​ዎን ምድር ትዘ​ረ​ፋ​ለች፤ የማ​ረ​ኳ​ትም ሁሉ ይጠ​ግ​ባሉ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
11“ርስ​ቴን የም​ት​በ​ዘ​ብዙ እና​ንተ ሆይ! ደስ ብሎ​አ​ች​ኋ​ልና፥ ሐሤ​ት​ንም አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ በመ​ስክ ላይም እን​ዳ​ለች ጊደር ሆና​ችሁ ተቀ​ና​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ብር​ቱ​ዎ​ችም በሬ​ዎች#ዕብ. “ፈረ​ሶች” ይላል። ቷጋ​ላ​ች​ሁና፤ 12እና​ታ​ችሁ እጅግ ታፍ​ራ​ለች፤ የወ​ለ​ደ​ቻ​ች​ሁም ትጐ​ሰ​ቍ​ላ​ለች፤ እነሆ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኋለ​ኛ​ዪቱ ትሆ​ና​ለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር፥ በረ​ሀም ትሆ​ና​ለች። 13ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ የተ​ነሣ ባድማ ትሆ​ና​ለች እንጂ ሰው አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም በኩል የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ በመ​ጣ​ባ​ትም መቅ​ሠ​ፍት ሁሉ ያፍ​ዋ​ጫል።
14“እና​ንተ ቀስ​ትን የም​ት​ገ​ትሩ ሰዎች ሁሉ፥ በባ​ቢ​ሎን ላይ በዙ​ሪ​ያዋ ተሰ​ለፉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ሠር​ታ​ለ​ችና ወር​ው​ሩ​ባት፤ እር​ስ​ዋ​ንም ከመ​ው​ጋት ቸል አት​በሉ፤ 15እጆ​ችዋ ደክ​መ​ዋ​ልና ክበ​ቡ​አት፤ ግንቧ ወድ​ቋል፤ ቅጥ​ር​ዋም ፈር​ሶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀል ነውና ተበ​ቀ​ሏት፤ እንደ ሠራ​ች​ውም ሥሩ​ባት። 16ዘሪ​ው​ንና በመ​ከር ጊዜ ማጭድ የሚ​ይ​ዘ​ውን ከባ​ቢ​ሎን አጥፉ፤ ከአ​ረ​ማ​ዊው ሰይፍ ፊት የተ​ነሣ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ወገኑ ይመ​ለ​ሳል፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ሀገሩ ይሸ​ሻል።
17“እስ​ራ​ኤል የባ​ዘነ በግ ነው፤ አን​በ​ሶች አሳ​ደ​ዱት፤ መጀ​መ​ሪያ የአ​ሦር ንጉሥ በላው፥ በመ​ጨ​ረ​ሻም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር አጥ​ን​ቱን ቈረ​ጠ​መው።”#በግ​እዝ “አጥ​ንት” የሚል የለም። 18ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የአ​ሦ​ርን ንጉሥ እንደ ተበ​ቀ​ልሁ እን​ዲሁ እነሆ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉ​ሥና ምድ​ሩን እበ​ቀ​ላ​ለሁ። 19እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ ማሰ​ማ​ር​ያው እመ​ል​ሳ​ለሁ፥ በቀ​ር​ሜ​ሎ​ስና በባ​ሳን፥ በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ራና በገ​ለ​ዓ​ድም ይሰ​ማ​ራል፤ ነፍ​ሱም ትጠ​ግ​ባ​ለች። 20በዚያ ወራት በዚ​ያም ዘመን፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ዚ​ህን በም​ድር የተ​ረ​ፉ​ትን ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና የእ​ስ​ራ​ኤል በደል ይፈ​ለ​ጋል፤ አይ​ኖ​ር​ምም፤ የይ​ሁ​ዳም ኀጢ​አት ይፈ​ለ​ጋል፥ ምንም አይ​ገ​ኝም።
21“በላ​ይ​ዋና በሚ​ኖ​ሩ​ባት ላይ በም​ሬት ውጡ፤ ሰይፍ ሆይ! ተበ​ቀዪ፥ ፍጻ​ሜ​ያ​ቸ​ው​ንም አጥፊ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ሽ​ንም ሁሉ አድ​ርጊ።#ዕብ. “በም​ራ​ታ​ይም ምድር ላይ፥ በፋ​ቁ​ድም በሚ​ኖ​ሩት ላይ ውጣ ፤ ግደ​ላ​ቸው ፈጽ​መ​ህም አጥ​ፋ​ቸው ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ይላል። 22የሰ​ል​ፍና የታ​ላቅ ጥፋት ውካታ በም​ድር ላይ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር ላይ” ይላል። አለ። 23ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ፈ​ጫት መዶሻ እን​ዴት ደቀ​ቀች! እን​ዴ​ትስ ተሰ​በ​ረች! ባቢ​ሎ​ንስ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዴት ባድማ ሆነች! 24ባቢ​ሎን ሆይ! በመ​ከ​ራው ተይ​ዘሽ ጠፋሽ፤ አን​ቺም ይህ እን​ደ​መ​ጣ​ብሽ አላ​ወ​ቅ​ሽም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​መ​ሽ​ዋ​ልና ተገ​ኝ​ተ​ሻል፤ ተይ​ዘ​ሽ​ማል።#ዕብ. “ባቢ​ሎን ሆይ! አጥ​ም​ጄ​ብ​ሻ​ለሁ ፤ አን​ቺም ሳታ​ውቂ ተይ​ዘ​ሻል ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ስለ ተዋ​ጋሽ ተገ​ኝ​ተ​ሻል ፤ ተይ​ዘ​ሽ​ማል” ይላል። 25የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር ይሠራ ዘንድ ሥራ አለ​ውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕቃ ቤቱን ከፍቶ የቍ​ጣ​ውን ዕቃ ጦር አው​ጥ​ቶ​አል። 26ጊዜዋ ደር​ሶ​አ​ልና ሣጥ​ኖ​ች​ዋን ከፍ​ታ​ችሁ እንደ ዋሻ በር​ብ​ሯት፤ ጨር​ሳ​ች​ሁም አጥ​ፏት፥ ምንም አታ​ስ​ቀ​ሩ​ላት። 27ፍሬ​ዋን ሁሉ አድ​ር​ቁ​ባት፤ ወደ መታ​ረ​ድም ይው​ረዱ፤ ቀና​ቸው ደር​ሳ​ለ​ችና፥ እነ​ሱን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ ደር​ሷ​ልና ወዮ​ላ​ቸው! 28የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በቀል፥ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም በቀል፥#“የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም በቀል” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በጽ​ዮን ይነ​ግሩ ዘንድ ሸሽ​ተው ከባ​ቢ​ሎን ሀገር ያመ​ለ​ጡት ሰዎች ድምፅ ተሰ​ም​ቶ​አል።
29“ቀስ​ትን የሚ​ገ​ትሩ ቀስ​ተ​ኞ​ችን ሁሉ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጥሩ​አ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያዋ ስፈ​ሩ​ባት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ሰዎች አንድ አያ​ም​ልጥ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​ማ​ለ​ችና እንደ ሥራዋ መጠን መል​ሱ​ላት፤ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ችም ሁሉ አድ​ር​ጉ​ባት። 30ስለ​ዚህ ጐበ​ዛ​ዝቷ በአ​ደ​ባ​ባ​ይዋ ላይ ይወ​ድ​ቃሉ፤ በዚ​ያም ቀን ሰል​ፈ​ኞ​ችዋ ሁሉ ይጠ​ፋሉ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 31ትዕ​ቢ​ተኛ ሆይ! አን​ቺን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ፥ ቀንሽ ደር​ሶ​አ​ልና እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 32አንቺ ትዕ​ቢ​ተኛ ሆይ!፥ ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፤ ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለ​ሽም፤ የሚ​ያ​ነ​ሳ​ሽም የለም፤ በዛ​ፎ​ችሽ#ዕብ. “በከ​ተ​ሞ​ችሽ” ይላል። ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያሽ ያለ​ው​ንም ሁሉ ትበ​ላ​ለች።”
33የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የይ​ሁዳ ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ተገ​ፍ​ተ​ዋል፤ የማ​ረ​ኩ​አ​ቸ​ውም ሁሉ በኀ​ይል ይይ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ይለ​ቅ​ቁ​አ​ቸ​ውም ዘንድ እንቢ ብለ​ዋል። 34የሚ​ቤ​ዢ​አ​ቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ምድ​ርን ያሳ​ርፍ ዘንድ፥ በባ​ቢ​ሎ​ንም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ያውክ ዘንድ ጠላ​ቶ​ቹን ወቀሳ ይወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋል። 35ሰይፍ በከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንና በባ​ቢ​ሎን በሚ​ኖሩ ላይ፥ በመ​ሳ​ፍ​ን​ቶ​ች​ዋና በጥ​በ​በ​ኞ​ችዋ ላይ አለ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 36ሰይፍ በተ​ዋ​ጊ​ዎ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ክ​ማሉ። ሰይ​ፍም በኀ​ያ​ላ​ኖ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ። 37ሰይፍ በፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውና በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸው ላይ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም በተ​ቀ​ላ​ቀሉ ሕዝብ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም እንደ ሴቶች ይሆ​ናሉ፤ ሰይፍ በመ​ዝ​ገ​ቦ​ችዋ ላይ አለ፤ ይበ​ተ​ና​ሉም። 38እር​ስዋ የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች ምድር ናትና፥ እነ​ር​ሱም በደ​ሴ​ቶ​ችዋ#ዕብ. “በጣ​ዖ​ታት” ይላል። ይመ​ካ​ሉና ሰይፍ በው​ኆ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ር​ቃሉ። 39ስለ​ዚህ የዱር አራ​ዊት ከተ​ኵ​ላ​ዎች ጋር ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ሰጎ​ኖ​ችም ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም፤ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚ​ኖ​ር​ባት የለም።#ምዕ. 50 ቍ. 39 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የተ​ለየ ነው። 40ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ከተ​ሞች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዲሁ ሰው በዚያ አይ​ቀ​መ​ጥም፤ የሰ​ውም ልጅ አይ​ኖ​ር​ባ​ትም።
41“እነሆ ሕዝብ ከሰ​ሜን ይመ​ጣል፤ ታላቅ ሕዝ​ብና ብዙ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣሉ። 42ቀስ​ትና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ይተ​ም​ማል፤ በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የባ​ቢ​ሎን ሴት ልጅ ሆይ እንደ እሳት በአ​ንቺ ላይ ይሰ​ለ​ፋሉ። 43የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ውካ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ቶ​አል፤ እጁም ደክ​ማ​ለች፤ ምጥ ወላድ ሴትን እን​ደ​ሚ​ይ​ዛ​ትም ጭን​ቀት ይዞ​ታል፤ 44እነሆ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ በቶሎ አባ​ር​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና እንደ አን​በሳ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ወደ ኤታም ምድር ይወ​ጣል፤ ጐል​ማ​ሶ​ቹ​ንም ሁሉ በእ​ር​ስዋ ላይ እሾ​ማ​ለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚ​ወ​ስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚ​ቋ​ቋም እረኛ ማን ነው? 45ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ቢ​ሎን ላይ የመ​ከ​ረ​ባ​ትን ምክር፥ በከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ላይ ያሰ​ባ​ትን ዐሳብ ስሙ፤ በእ​ው​ነት የበ​ጎ​ቻ​ቸ​ቸው ጠቦ​ቶች ይጠ​ፋሉ፤ በእ​ው​ነት ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ባድማ ይሆ​ናሉ። 46ባቢ​ሎ​ንን ከያ​ዝ​ዋት ሰዎች ድምፅ የተ​ነሣ ምድር ተና​ወ​ጠች፤ ጩኸ​ትም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ተሰማ።”#ምዕ. 50 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 27 ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ