መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 6:7-16

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 6:7-16 አማ2000

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በም​ድ​ያም ምክ​ን​ያት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጮኹ ጊዜ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ነቢይ ላከ፤ እር​ሱም አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ኋ​ችሁ፤ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት አስ​ለ​ቀ​ቅ​ኋ​ችሁ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ ከሚ​ጋ​ፉ​አ​ች​ሁም ሁሉ እጅ አዳ​ን​ኋ​ችሁ፤ ከፊ​ታ​ች​ሁም አሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው፤ ሀገ​ራ​ቸ​ው​ንም ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ እና​ን​ተ​ንም፦ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ በም​ድ​ራ​ቸው የተ​ቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አማ​ል​ክት አት​ፍሩ አል​ኋ​ችሁ። እና​ንተ ግን ቃሌን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።” የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ መጥቶ በኤ​ፍ​ራታ ባለ​ችው ለኤ​ዝሪ አባት ለኢ​ዮ​አስ በነ​በ​ረ​ችው ዛፍ በታች ተቀ​መጠ፤ ልጁም ጌዴ​ዎን ከም​ድ​ያ​ማ​ው​ያን ለማ​ሸሽ በወ​ይን መጭ​መ​ቂ​ያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለእ​ርሱ ተገ​ልጦ፥ “አንተ ጽኑዕ ኀያል ሰው! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው” አለው። ጌዴ​ዎ​ንም፥ “ጌታዬ ሆይ! እሺ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረ​ሰ​ብን? አባ​ቶ​ቻ​ች​ንስ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ናል ብለው ይነ​ግ​ሩን የነ​በረ ተአ​ም​ራት ወዴት አለ? አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ናል፤ በም​ድ​ያም እጅም አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ናል” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ከ​ተና፥ “በዚህ በጕ​ል​በ​ትህ ሂድ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ከም​ድ​ያም እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ፤ እነሆ፥ ልኬ​ሃ​ለሁ” አለው። እር​ሱም፥ “ጌታ ሆይ! እሺ፥ እስ​ራ​ኤ​ልን በምን አድ​ና​ለሁ? ወገኔ በም​ናሴ ነገድ ዘንድ ጥቂ​ቶች ናቸው፤ እኔም በአ​ባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ምድ​ያ​ም​ንም እንደ አንድ ሰው አድ​ር​ገህ ታጠ​ፋ​ለህ” አለው።