የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓሊምንና አስታሮትን፥ የሶርያንም አማልክት፥ የሲዶናንም አማልክት፥ የሞዓብንም አማልክት፥ የአሞንንም ልጆች አማልክት፥ የፍልስጥኤማውያንንም አማልክት አመለኩ፤ እግዚአብሔርንም ተዉ፤ አላመለኩትምም። እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በፍልስጥኤማውያን እጅና በአሞን ልጆች እጅም አሳልፎ ሰጣቸው። በዚያም ጊዜ የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፤ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞሬዎናውያን ሀገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት አስጨነቁአቸው። የአሞንም ልጆች ከይሁዳ፥ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ እስራኤልም እጅግ ተጨነቁ። የእስራኤልም ልጆች፥ “አንተን አምላካችንን ትተን በዓሊምን አምልከናልና ኀጢአት ሠርተናል” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፥ “ግብፃውያን፥ አሞሬዎናውያንም፥ የአሞንና የሞአብም ልጆች፥ ፍልስጥኤማውያንም፥ ሲዶናውያንም፥ ምድያማውያንም፥ አማሌቃውያንም አላስጨነቋችሁምን? ወደ እኔም ጮኻችሁ፤ እኔም ከእጃቸው አዳንኋችሁ። እናንተ ግን ተዋችሁኝ፤ ሌሎችንም አማልክት አመለካችሁ፤ ስለዚህም ደግሞ አላድናችሁም። ሄዳችሁ ወደ መረጣችኋቸው አማልክት ጩኹ፤ እነርሱም በመከራችሁ ጊዜ ያድኑአችሁ።” የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን፥ “እኛ ኀጢአትን ሠርተናል፤ አንተ በፊትህ ደስ የሚያሰኝህን አድርግብን፤ ዛሬ ግን እባክህ አድነን” አሉት። ሌሎችንም አማልክት ከመካከላቸው አስወገዱ፤ እግዚአብሔርንም ብቻ አመለኩ፤ ደስም አሰኙት፤ የእስራኤልም ልጆች ከሥቃይ የተነሣ አእምሮአቸውን አጥተው ነበር።
መጽሐፈ መሳፍንት 10 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መሳፍንት 10:6-16
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች