ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 42:1-13

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 42:1-13 አማ2000

እነሆ፥ ደግፌ የያ​ዝ​ሁት ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ፤ ነፍሴ የተ​ቀ​በ​ለ​ችው ምርጤ እስ​ራ​ኤ​ልም፤ በእ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሴን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም ለአ​ሕ​ዛብ ፍር​ድን ያመ​ጣል። አይ​ጮ​ኽም፤ ቃሉ​ንም አያ​ነ​ሣም፤ ድም​ፁ​ንም በሜዳ አያ​ሰ​ማም። የተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ሸን​በ​ቆን አይ​ሰ​ብ​ርም፤ የሚ​ጤ​ስ​ንም ክር አያ​ጠ​ፋም፤ ነገር ግን በእ​ው​ነት ፍር​ድን ያመ​ጣል። በም​ድ​ርም ፍር​ድን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ያበ​ራል እንጂ አይ​ጠ​ፋም፤ አሕ​ዛ​ብም በስሙ ይታ​መ​ናሉ። ሰማ​ይን የፈ​ጠረ፥ የዘ​ረ​ጋ​ውም፥ ምድ​ር​ንና በው​ስ​ጥዋ ያለ​ውን ሁሉ ያጸና፥ በእ​ር​ስዋ ላይ ለሚ​ኖሩ ሕዝብ እስ​ት​ን​ፋ​ስን፥ ለሚ​ሄ​ዱ​ባ​ትም መን​ፈ​ስን የሚ​ሰጥ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ በጽ​ድቅ ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ጄም እይ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለ​ሁም፤ ለልጅ ልጅ ቃል ኪዳን፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ብር​ሃን አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። የዕ​ው​ራ​ን​ንም ዐይን ትከ​ፍት ዘንድ፥ የተ​ጋ​ዙ​ት​ንም ከግ​ዞት ቤት፥ በጨ​ለ​ማም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከወ​ህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብ​ሬን ለሌላ፥ ምስ​ጋ​ና​ዬ​ንም ለተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች አል​ሰ​ጥም። እነሆ የቀ​ድ​ሞው ነገር ተፈ​ጸመ፤ አዲስ ነገ​ር​ንም እና​ገ​ራ​ለሁ፤ አስ​ቀ​ድ​ሞም ሳይ​ነ​ገር እር​ሱን አስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።” ወደ ባሕር የም​ት​ወ​ርዱ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ውስጥ የም​ት​ጓዙ ሁሉ፥ ደሴ​ቶ​ችና በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ መዝ​ሙር ዘምሩ፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ስሙን አክ​ብሩ። ምድረ በዳ​ውና ከተ​ሞ​ችዋ፥ የቄ​ዳ​ርም ነዋ​ሪ​ዎ​ችና መን​ደ​ሮች ድም​ፃ​ቸ​ውን ያንሡ፤ በዋ​ሻም የሚ​ኖሩ እልል ይበሉ፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርን ይስጡ፤ ምስ​ጋ​ና​ው​ንም በደ​ሴ​ቶች ይና​ገሩ። የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወ​ጣል፤ ኀይ​ለ​ኛ​ው​ንም ያጠ​ፋል፤ ቅን​አ​ት​ንም ያስ​ነ​ሣል፤ በጠ​ላ​ቶ​ቹም ላይ በኀ​ይል ይጮ​ኻል።