ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 8:7-13

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 8:7-13 አማ2000

ፊተ​ኛ​ይቱ ያለ ነቀፋ ብት​ሆን ኖሮ ሁለ​ተ​ኛ​ይ​ቱን ባል​ፈ​ለ​ገም ነበር። ነገር ግን እነ​ር​ሱን ነቅፎ እን​ዲህ አለ፥ “እነሆ፥ ለቤተ እስ​ራ​ኤ​ልና ለቤተ ይሁ​ዳም አዲስ ኪዳን የም​ሠ​ራ​በት ዘመን ይመ​ጣል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። እጃ​ቸ​ውን ይዤ ከም​ድረ ግብፅ ባወ​ጣ​ኋ​ቸው ጊዜ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ገባ​ሁት እን​ደ​ዚያ ያለ ኪዳን አይ​ደ​ለም፤ እነ​ርሱ በኪ​ዳኔ አል​ኖ​ሩ​ምና፤ እኔም ቸል ብያ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ከእ​ነ​ዚያ ዘመ​ናት በኋላ ለቤተ እስ​ራ​ኤል የም​ገ​ባው ቃል ይህ ነው፦ ሕጌን በል​ባ​ቸው አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ በሕ​ሊ​ና​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። እን​ግ​ዲህ አንዱ ሌላ​ውን አያ​ስ​ተ​ም​ርም፤ ወን​ድ​ምም ወን​ድ​ሙን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕወቅ ብሎ አያ​ስ​ተ​ም​ርም፤ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያው​ቁ​ኛ​ልና። ዐመ​ፃ​ቸ​ውን እም​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ደግሜ አላ​ስ​ብም።” አዲስ ትእ​ዛዝ በማ​ለቱ የቀ​ደ​መ​ች​ቱን አስ​ረ​ጃት፤ አሮ​ጌና ውራጅ የሆ​ነ​ውስ ለጥ​ፋት የቀ​ረበ ነው።