ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 4:1-5

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 4:1-5 አማ2000

አዳ​ምም ሚስ​ቱን ሔዋ​ንን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ቃየ​ል​ንም ወለ​ደ​ችው። እር​ስ​ዋም “ወንድ ልጅ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ኘሁ” አለች። ደግ​ሞም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን ወለ​ደ​ችው። አቤ​ልም በግ ጠባቂ ሆነ፤ ቃየ​ልም ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሆነ። ከብዙ ቀን በኋ​ላም እን​ዲህ ሆነ፤ ቃየል ከም​ድር ፍሬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ፤ አቤ​ልም ደግሞ ከበ​ጎቹ መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ው​ንና ከሰ​ቡት አቀ​ረበ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ አቤ​ልና ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ተመ​ለ​ከተ፤ ወደ ቃየ​ልና ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ግን አል​ተ​መ​ለ​ከ​ተም። ቃየ​ል​ንም እጅግ አሳ​ዘ​ነው፤ ፊቱም ጠቈረ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}