ወደ ገላ​ትያ ሰዎች 5:7-14

ወደ ገላ​ትያ ሰዎች 5:7-14 አማ2000

ቀድ​ሞስ በመ​ል​ካም ተፋ​ጥ​ና​ችሁ ነበር፤ በእ​ው​ነት እን​ዳ​ታ​ምኑ ማን አሰ​ና​ከ​ላ​ችሁ? ይህ መፋ​ጠ​ና​ችሁ ከሚ​ጠ​ራ​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምና። ጥቂት እርሾ ብዙ​ውን ዱቄት መጻጻ ያደ​ር​ገው የለ​ምን? እኔ ሌላ እን​ዳ​ታ​ስቡ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አም​ኛ​ችሁ ነበር፤ የሚ​ያ​ው​ካ​ችሁ ግን የሆ​ነው ቢሆን ፍዳ​ውን ይሸ​ከ​ማል። ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔ ግዝ​ረ​ትን ገና የም​ሰ​ብክ ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ለምን ያሳ​ድ​ዱ​ኛል? እን​ግ​ዲህ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ተግ​ዳ​ሮት እን​ዲ​ያው ቀር​ቶ​አል። የሚ​ያ​ው​ኩ​አ​ች​ሁም ሊለዩ ይገ​ባል። ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ን​ተስ ለነ​ጻ​ነት ተጠ​ር​ታ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ ለነ​ጻ​ነ​ታ​ችሁ ምክ​ን​ያት አታ​ድ​ር​ጉ​ላት፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም በፍ​ቅር ተገዙ። “ወን​ድ​ም​ህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚ​ለው አንድ ቃል ሕግን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማ​ልና።