ወደ ገላ​ትያ ሰዎች 2:14-21

ወደ ገላ​ትያ ሰዎች 2:14-21 አማ2000

ነገር ግን ወደ እው​ነ​ተ​ኛው ወን​ጌል እግ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ላ​ቀኑ ባየሁ ጊዜ፥ በሰው ሁሉ ፊት ኬፋን እን​ዲህ አል​ሁት፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን በአ​ይ​ሁድ ሥር​ዐት ያይ​ደለ፥ በአ​ረ​ማ​ው​ያን ሥር​ዐት የም​ት​ኖር ከሆነ እን​ግ​ዲህ አይ​ሁድ እን​ዲ​ሆኑ አረ​ማ​ው​ያ​ንን ለምን ታስ​ገ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ?” እኛ በት​ው​ል​ዳ​ችን አይ​ሁድ ነን፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞች የሆኑ አሕ​ዛ​ብም አይ​ደ​ለ​ንም። ሰው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን እንጂ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት እን​ደ​ማ​ይ​ጸ​ድቅ እና​ው​ቃ​ለ​ንና፤ እኛም የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ሳይ​ሆን በእ​ርሱ በማ​መ​ና​ችን እን​ጸ​ድቅ ዘንድ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አም​ነ​ናል፤ ሰው ሁሉ በኦ​ሪት ሥራ አይ​ጸ​ድ​ቅ​ምና። በክ​ር​ስ​ቶስ ልን​ጸ​ድቅ የም​ንሻ እኛ እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ከሆን እን​ግ​ዲህ ክር​ስ​ቶስ የኀ​ጢ​አት አገ​ል​ጋይ መሆኑ ነውን? አይ​ደ​ለም። ያን ያፈ​ረ​ስ​ሁ​ትን መልሼ የማ​ንጽ ከሆነ ራሴን ሕግ አፍ​ራሽ አደ​ረ​ግሁ። እኔስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያው ሆኜ በሁ​ለ​ተ​ኛው ሕግ እኖር ዘንድ ከቀ​ደ​መው ሕግ ተለ​የሁ። ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋርም ተሰ​ቀ​ልሁ፤ ሕይ​ወ​ቴም አለ​ቀች፤ ነገር ግን በክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወት አለሁ፤ ዛሬም በሥ​ጋዬ የም​ኖ​ረ​ውን ኑሮ የወ​ደ​ደ​ኝን ስለ እኔም ራሱን አሳ​ልፎ የሰ​ጠ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ በማ​መን እኖ​ራ​ለሁ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ አል​ክ​ድም፤ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት የሚ​ጸ​ድቁ ከሆነ እን​ኪ​ያስ ክር​ስ​ቶስ በከ​ንቱ ሞተ።