መጽሐፈ ዕዝራ 2
2
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ የአይሁድ ስም ዝርዝር
(ነህ. 7፥4-73)
1የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው። 2ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከሮሃልያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጎዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ 3የፋሮስ ልጆች ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት። 4የሰፋጥያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። 5የኤራስ ልጆች ሰባት መቶ ሰባ አምስት። 6ከያሱኤና ከዮአብ ልጆች የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ልጆች ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዐሥራ ሁለት። 7የኤላም ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 8የዛቱዕ ልጆች ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት። 9የዘካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ። 10የባኒ ልጆች ስድስት መቶ አርባ ሁለት። 11የቢባይ ልጆች ስድስት መቶ ሃያ ሦስት። 12የዓዝጋድ ልጆች ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ሁለት። 13የአዶኒቃም ልጆች ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት። 14የበጕዋይ ልጆች ሁለት ሺህ አምሳ ስድስት። 15የዓዲን ልጆች አራት መቶ አምሳ አራት። 16ከሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች ዘጠና ስምንት። 17የቤሳይ ልጆች ሦስት መቶ ሃያ ሦስት። 18የዮራ ልጆች መቶ ዐሥራ ሁለት። 19የሐሱም ልጆች ሁለት መቶ ሃያ ሦስት። 20የጋቤር ልጆች ዘጠና አምስት። 21የቤተ ልሔም ልጆች መቶ ሃያ ሦስት። 22የነጦፋ ልጆች አምሳ ስድስት። 23የዓናቶት ልጆች መቶ ሃያ ስምንት። 24የዓዝሞት ልጆች አርባ ሁለት። 25የቂርያትይዓሪምና የቃፌር፥ የብኤሮትም ልጆች ሰባት መቶ አርባ ሦስት። 26የራማና የጋባዕ ልጆች ስድስት መቶ ሃያ አንድ። 27የመኪማስ ሰዎች መቶ ሃያ ሁለት። 28የቤቴልና የጋይ ሰዎች ሁለት መቶ ሃያ ሦስት። 29የናባው ልጆች አምሳ ሁለት። 30የመጌባስ ልጆች መቶ አምሳ ስድስት። 31የኤላማር ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 32የኤላም ልጆች ሦስት መቶ ሃያ። 33የሎድ፥ የሐዲድና የኦኖም ልጆች ሰባት መቶ ሃያ አምስት። 34የኢያሪኮ ልጆች ሦስት መቶ አርባ አምስት። 35የሴዓናህ ልጆች ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ። 36ካህናቱ ከኢያሱ ወገን የዮዳኤ ልጆች ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። 37የኢሜር ልጆች ሺህ አምሳ ሁለት። 38የፋስኮር ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። 39የኤረም ልጆች ሺህ ዐሥራ ሰባት።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አንድ ሽህ ሰባት” ይላል።
40ሌዋውያኑ፤ ከሁድያ ልጆች ወገን የኢዮስስና የቀዳምሔል ልጆች ሰባ አራት።
41መዘምራኑ የአሳፍ ልጆች መቶ ሃያ ስምንት።
42የበረኞች ልጆች፥ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሰበዋይ ልጆች ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ።
43ናታኒም፤ የሲሓ ልጆች፥ የሐሡፊ ልጆች፥ የጠብዖት ልጆች፤ 44የቃዴስ ልጆች፥ የሲሔል ልጆች፥ የፋዶን ልጆች፤ 45የልባና ልጆች፥ የአጋባ ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ 46የአጋብ ልጆች፥ የሰላሚ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፤ 47የጋዱል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ የራእያ ልጆች፤ 48የረአሶን ልጆች፥ የኒቆዳ ልጆች፥ የጋሴም ልጆች፤ 49የዓዝያት ልጆች፥ የፋሒስ ልጆች፥ የባሲ ልጆች፤ 50የአሲና ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥ የናፌሶን ልጆች፤ 51የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቁፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፤ 52የበስሎት ልጆች፥ የማሁድ ልጆች፥ የአሪስ ልጆች፤ 53የበርቆስ ልጆች፥ የሲሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥ 54የንስያ ልጆች፥ የአጡፋ ልጆች።
55የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች፤ የሳጢ ልጆች፥ የሰፌርታ ልጆች፥ የፋዱርሓ ልጆች፤ 56የኢያሔል ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፤ 57የሰፋጥያስ ልጆች፥ የአጤል ልጆች፥ የፎኬርት ልጆች፥ የሐፂባይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች። 58እነዚህ ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።
59ከቲልሜላ፥ ከቴላርሳ፥ ከክሩብ፥ ከሐዳን፥ ከኤሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፤ 60የዳላያ ልጆች፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የቡኣ ልጆች” የሚል ይጨምራል። የጦብያ ልጆች፥ የኒቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት ነበሩ። 61ከካህናቱም ልጆች፤ የአብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስማቸውም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች። 62እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አልተገኘም፤ ከክህነትም ተከለከሉ። 63ሐቲርሰስታም፥ “በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ድረስ ከቅዱሰ ቅዱሳኑ አትበሉም” አላቸው።
64ጉባኤው ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ። 65ይኸውም ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ሁለት መቶ ወንዶች መዘምራንና ሴቶች መዘምራትም ነበሩአቸው። 66ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት፥ በቅሎዎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፥ 67ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ነበሩ።
68በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአባቶች ቤቶች አለቆች አያሌዎች ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው ይሠሩት ዘንድ በፈቃዳቸው ሰጡ። 69ስድሳ አንድ ሺህም የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካህናት ልብስ እንደ ችሎታቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ።
70ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ ከሕዝቡም አያሌዎች፥ መዘምራኑና በረኞቹም፥ ናታኒምም በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዕዝራ 2: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ