ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 2:13-18

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 2:13-18 አማ2000

አሁን ግን ቀድሞ ርቃ​ችሁ የነ​በ​ራ​ችሁ እና​ንተ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆና​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ደም ቀረ​ባ​ችሁ። ሁለ​ቱን አንድ ያደ​ረገ ሰላ​ማ​ችን እርሱ ነውና፥ በሥ​ጋ​ውም በመ​ካ​ከል የነ​በ​ረ​ውን የጥል ግድ​ግዳ አፍ​ርሶ ጥልን ሻረ። ሁለ​ቱ​ንም አድሶ አንድ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ በሥ​ር​ዐቱ የት​እ​ዛ​ዝን ሕግ አጠፋ፤ ዕር​ቅ​ንም አደ​ረገ። በመ​ስ​ቀ​ሉም በአ​ንድ ሥጋው ሁለ​ቱን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ በእ​ር​ሱም ጥልን አጠፋ። መጥ​ቶም፤ ቀር​በን ለነ​በ​ር​ነው ሰላ​ምን፥ ርቃ​ችሁ ለነ​በ​ራ​ች​ሁት ለእ​ና​ን​ተም ሰላ​ምን ሰጠን። እርሱ መር​ቶ​ና​ልና፤ ሁለ​ታ​ች​ን​ንም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ወደ አባቱ አቅ​ር​ቦ​ና​ልና።

ከ ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 2:13-18ጋር የተዛመዱ ነፃ የንባብ እቅዶች እና ምንባቦች