ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 1:4-10

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 1:4-10 አማ2000

ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር በፊቱ ቅዱ​ሳን፥ ንጹ​ሓ​ንና ያለ ነውር በፍ​ቅር ያደ​ር​ገን ዘንድ ለእ​ርሱ መረ​ጠን። በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም እንደ ውድ ፈቃዱ ለእ​ርሱ ልጆች ልን​ሆን አስ​ቀ​ድሞ ወሰ​ነን። በሚ​ወ​ደው ልጁ የሰ​ጠን የጸ​ጋው ክብር ይመ​ሰ​ገን ዘንድ። በእ​ር​ሱም እንደ ቸር​ነቱ ብዛት በደሙ ድኅ​ነ​ትን አገ​ኘን፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም ተሰ​ረ​የ​ልን። ይኸ​ውም በፍ​ጹም ጥበ​ብና ምክር ለእኛ አብ​ዝቶ ያደ​ረ​ገው ነው። እንደ ወደ​ደም በእ​ርሱ የወ​ሰ​ነ​ውን፥ የፈ​ቃ​ዱን ምሥ​ጢር ገለ​ጠ​ልን። የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ት​ንም ጊዜ​ውን ወሰነ፤ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያለ​ውም ሁሉ ይታ​ደስ ዘንድ ክር​ስ​ቶ​ስን በሁሉ ላይ አላ​ቀው።