ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 1:19-21

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 1:19-21 አማ2000

በክ​ር​ስ​ቶስ እንደ አደ​ረ​ገው እንደ ከሃ​ሊ​ነቱ ታላ​ቅ​ነት በም​ና​ምን በእኛ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው የከ​ሃ​ሊ​ነቱ ጽናት ብዛት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ ነው። ከሙ​ታን ለይቶ ባስ​ነ​ሣው፥ በሰ​ማ​ይም በቀኙ ባስ​ቀ​መ​ጠው፥ ከመ​ላ​እ​ክት ሁሉ በላይ ከመ​ኳ​ን​ን​ትና ከኀ​ይ​ላት፥ ከአ​ጋ​እ​ዝ​ትና ከሚ​ጠ​ራ​ውም ስም ሁሉ በላይ፥ በዚህ ዓለም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በሚ​መ​ጣ​ውም ዓለም እንጂ።