ኦሪት ዘዳ​ግም 7:6-8

ኦሪት ዘዳ​ግም 7:6-8 አማ2000

“ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፤ በም​ድር ፊት ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ይልቅ ለእ​ርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆ​ን​ለት ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​ሃ​ልና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የመ​ረ​ጣ​ችሁ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ስለ በዛ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ እና​ንት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ጥቂ​ቶች ነበ​ራ​ች​ሁና፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ እጅ፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ አወ​ጣ​ችሁ፤ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖን እጅ አዳ​ና​ችሁ።