የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 9:26-43

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 9:26-43 አማ2000

ሳው​ልም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረሰ ጊዜ ሊገ​ና​ኛ​ቸው ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን ፈለ​ጋ​ቸው። ሁሉም ፈሩት፤ የጌ​ታ​ችን ደቀ መዝ​ሙር እንደ ሆነ አላ​መ​ኑ​ትም ነበ​ርና። በር​ና​ባ​ስም አግ​ኝቶ ወደ ሐዋ​ር​ያት ወሰ​ደው፤ ጌታ​ች​ንም በመ​ን​ገድ እንደ ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና እንደ አነ​ጋ​ገ​ረው፥ በደ​ማ​ስ​ቆም በኢ​የ​ሱስ ስም እንደ አስ​ተ​ማረ ነገ​ራ​ቸው። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አብ​ሮ​አ​ቸው ይገ​ባና ይወጣ ነበረ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ስምም በግ​ልጥ ያስ​ተ​ምር ነበር። ከግ​ሪክ ሀገር መጥ​ተው የነ​በ​ሩ​ት​ንም አይ​ሁድ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ሊገ​ድ​ሉት ፈለጉ። ወን​ድ​ሞ​ችም ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሳ​ርያ አወ​ረ​ዱት፤ ከዚ​ያም ወደ ጠር​ሴስ ላኩት። በይ​ሁዳ፥ በሰ​ማ​ር​ያና በገ​ሊላ ያሉ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ በሰ​ላም ኖሩ፤ ታነ​ጹም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት ጸን​ተው ኖሩ፤ ሕዝ​ቡም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ አጽ​ና​ኝ​ነት በዙ። ከዚ​ህም በኋላ ጴጥ​ሮስ በየ​ቦ​ታዉ ሲዘ​ዋ​ወር በልዳ ወደ​ሚ​ኖ​ሩት ቅዱ​ሳን ዘንድ ደረሰ። በዚ​ያም ኤንያ የተ​ሰኘ ሰውን አገኘ፤ እር​ሱም ታሞ በአ​ልጋ ከተኛ ስም​ንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ ሽባ ነበ​ርና። ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ኤንያ ሆይ፥ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ይፈ​ው​ስህ፤ ተነ​ሥና አል​ጋ​ህን አን​ጥፍ” አለው፤ ያን​ጊ​ዜም ተነሣ። በል​ዳና በሳ​ሮና የሚ​ኖ​ሩም ሁሉ እር​ሱን አይ​ተው ወደ ጌታ​ችን ተመ​ለሱ። በኢ​ዮጴ ሀገ​ርም ጣቢታ የም​ት​ባል አን​ዲት ደቀ መዝ​ሙር ነበ​ረች፤ በት​ር​ጓ​ሜ​ውም ዶር​ቃስ ይሉ​አ​ታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እር​ስ​ዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽ​ዋ​ትም ትሰጥ ነበር። ያን​ጊ​ዜም ታማ ሞተ​ችና በድ​ን​ዋን አጥ​በው በሰ​ገ​ነት አስ​ተ​ኙ​አት። ልዳም ለኢ​ዮጴ ቅርብ ነበ​ርና ደቀ መዛ​ሙ​ርት ጴጥ​ሮስ በዚያ እን​ዳለ ሰም​ተው ወደ እነ​ርሱ መም​ጣት እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ ይማ​ል​ዱት ዘንድ ሁለት ሰዎ​ችን ወደ እርሱ ላኩ። ጴጥ​ሮ​ስም ተነ​ሥቶ አብ​ሮ​አ​ቸው ሄደ፤ በደ​ረ​ሰም ጊዜ ወደ ሰገ​ነት አወ​ጡት፤ ባል​ቴ​ቶ​ችም ሁሉ ወደ እርሱ መጥ​ተው በፊቱ ቆሙ፤ ያለ​ቅ​ሱ​ላ​ትም ነበር፤ ዶር​ቃ​ስም በሕ​ይ​ወት ሳለች የሠ​ራ​ች​ውን ቀሚ​ሱ​ንና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን አሳ​ዩት። ጴጥ​ሮ​ስም ሁሉን ካስ​ወጣ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ ጸለየ፤ ወደ በድ​ን​ዋም መለስ ብሎ፥ “ጣቢታ ሆይ፥ ተነሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም ዐይ​ኖ​ች​ዋን ገለ​ጠች፤ ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮ​ስን አየ​ችው፤ ቀና ብላም ተቀ​መ​ጠች። እጁ​ንም ለእ​ር​ስዋ ሰጥቶ አስ​ነ​ሣት፤ ቅዱ​ሳ​ን​ንና ባል​ቴ​ቶ​ች​ንም ጠርቶ እር​ስ​ዋን አድኖ ሰጣ​ቸው። በኢ​ዮ​ጴም ያሉ ሁሉ ይህን ሰሙ፤ ብዙ​ዎ​ችም በጌ​ታ​ችን አመኑ። ጴጥ​ሮ​ስም በኢ​ዮጴ በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት ብዙ ቀን ተቀ​መጠ።