የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 4:13-22

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 4:13-22 አማ2000

ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ግልጥ አድ​ር​ገው ሲና​ገሩ ባዩ​አ​ቸው ጊዜ፥ ያል​ተ​ማ​ሩና መጽ​ሐ​ፍን የማ​ያ​ውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐው​ቀው አደ​ነቁ፤ ሁል​ጊ​ዜም ከኢ​የ​ሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ። ያን የዳ​ነ​ውን ሰውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቆሞ በአ​ዩት ጊዜ የሚ​ሉ​ትን አጡ። ከሸ​ን​ጎ​ውም ጥቂት ፈቀቅ አደ​ረ​ጉ​አ​ቸ​ውና እርስ በር​ሳ​ቸው ተነ​ጋ​ገሩ። እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እነ​ዚ​ህን ሰዎች ምን እና​ድ​ር​ጋ​ቸው? እነሆ፥ በእ​ነ​ርሱ የሚ​ደ​ረ​ገው ተአ​ምር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ዘንድ ታወቀ፤ ግል​ጥም ሆነ፤ ልን​ሰ​ው​ረ​ውም አን​ች​ልም። ነገር ግን በሕ​ዝቡ ዘንድ እጅግ እን​ዳ​ይ​ስ​ፋፋ ዳግ​መኛ በኢ​የ​ሱስ ስም ሰውን እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ምሩ አጠ​ን​ክ​ረን እን​ገ​ሥ​ጻ​ቸው።” ጠር​ተ​ውም፦“ በኢ​የ​ሱስ ስም ፈጽሞ አት​ና​ገሩ አታ​ስ​ተ​ም​ሩም” ብለው አዘ​ዙ​አ​ቸው። ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያይ​ደለ እና​ን​ተን ልን​ሰማ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይገ​ባ​ልን? እስኪ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ። እኛስ ያየ​ነ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ከመ​ና​ገር ዝም እንል ዘንድ አን​ች​ልም።” እነ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቀ​ጡ​በት ምክ​ን​ያት ስለ አጡ​ባ​ቸው ገሥ​ጸው ለቀ​ቁ​አ​ቸው፤ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ምር ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበ​ርና። ይህ የድ​ኅ​ነት ምል​ክት ለተ​ደ​ረ​ገ​ለት ለዚያ ሰው ከአ​ርባ ዓመት ይበ​ል​ጠው ነበ​ረና።