የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 23:9-11

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 23:9-11 አማ2000

ታላቅ ውካ​ታም ሆነ፤ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ወገን የሆኑ ጸሐ​ፍት ተነ​ሥ​ተው ይጣ​ሉና ይከ​ራ​ከሩ ጀመሩ፤ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ነው ክፉ ነገር የለም፤ መን​ፈስ ወይም መል​አክ ተና​ግ​ሮት እንደ ሆነ እንጃ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አን​ጣላ” አሉ። እጅ​ግም በታ​ወኩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስን እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቁት የሻ​ለ​ቃው ፈራና መጥ​ተው ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አው​ጥ​ተው ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ወታ​ደ​ሮ​ቹን አዘዘ። በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሌሊት ጌታ​ችን ለጳ​ው​ሎስ ተገ​ልጦ፥ “ጽና፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምስ​ክር እንደ ሆን​ኸኝ እን​ዲሁ በሮም ምስ​ክር ትሆ​ነ​ኛ​ለህ” አለው።