ሐዋርያትና ቀሳውስትም ስለዚህ ነገር የሚያደርጉትን ያዩ ዘንድ ተሰበሰቡ። ብዙ ክርክርም ከተከራከሩ በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፥ “ወንድሞች ሆይ፥ ስሙ፤ ለአሕዛብ ከአፌ የወንጌሉን ቃል እንዳሰማቸውና እንዲያምኑ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንደ መረጠኝ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። ልብን የሚያውቅ እግዚአብሔርም ለእኛ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው። ልባቸውንም በእምነት አንጽቶ ከእኛ አልለያቸውም። አሁንም እግዚአብሔርን አትፈታተኑት፤ እኛም አባቶቻችንም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ ለምን ትጭናላችሁ? ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንድን ዘንድ እንታመናለን፤ እነርሱም እንደ እኛ ይድናሉ።”
የሐዋርያት ሥራ 15 ያንብቡ
ያዳምጡ የሐዋርያት ሥራ 15
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሐዋርያት ሥራ 15:6-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች