የሳኦልም ልጅ ኢያቡስቴ አበኔር በኬብሮን እንደ ሞተ ሰማ፤ እጆቹም ደከሙ፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ደነገጡ። ለሳኦልም ልጅ ለኢያቡስቴ የጭፍራ አለቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ የአንደኛው ስም በዓና፥ የሁለተኛውም ስም ሬካብ ነበረ፤ ከብንያምም ልጆች የቤሮታዊው የሬሞን ልጆች ነበሩ፤ ቤሮትም ለብንያም ተቈጥራ ነበር። ቤሮታውያንም ወደ ጌቴም ሸሽተው ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ተጠግተው ነበር።
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ 4 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ 4:1-3
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች