መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 4:1-3

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 4:1-3 አማ2000

የሳ​ኦ​ልም ልጅ ኢያ​ቡ​ስቴ አበ​ኔር በኬ​ብ​ሮን እንደ ሞተ ሰማ፤ እጆ​ቹም ደከሙ፤ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ሁሉ ደነ​ገጡ። ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለኢ​ያ​ቡ​ስቴ የጭ​ፍራ አለ​ቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ደ​ኛው ስም በዓና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሬካብ ነበረ፤ ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች የቤ​ሮ​ታ​ዊው የሬ​ሞን ልጆች ነበሩ፤ ቤሮ​ትም ለብ​ን​ያም ተቈ​ጥራ ነበር። ቤሮ​ታ​ው​ያ​ንም ወደ ጌቴም ሸሽ​ተው ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ተጠ​ግ​ተው ነበር።