ንጉሡ ዳዊትም ወደ በውሪም መጣ፤ እነሆም፥ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየሄደም ይረግመው ነበር። ወደ ዳዊትና ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት አገልጋዮችም ድንጋይ ይወረውር ነበር፤ በንጉሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኀያላኑ ሁሉ ነበሩ። ሳሚም ሲረግመው እንዲህ ይል ነበር፥ “ውጣ! አንተ የደም ሰውና ዐመፀኛ ሰው ሂድ! ሂድ! በፋንታው ነግሠሃልና እግዚአብሔር የሳኦልን ቤት ደም ሁሉ መለሰብህ፤ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ለልጅህ ለአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ እነሆም፥ አንተ የደም ሰው ነህና በመከራ ተይዘሃል።” የሶርህያ ልጅ አቢሳም ንጉሡን አለው፥ “ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን ስለምን ይረግማል? ልሻገርና ራሱን ልቍረጠው፤” ንጉሡም፥ “እናንተ የሶርህያ ልጆች! በእኔና በእናንተ መካከል ምን አለኝ? እግዚአብሔር ዳዊትን ርገመው ብሎ አዝዞታልና ይርገመኝ፤ ለምንስ እንዲህ ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?” አለ። ዳዊትም አቢሳንና አገልጋዮቹን ሁሉ፥ “እነሆ፥ ከወገቤ የወጣው ልጄ ነፍሴን ይሻል፤ ይልቁንስ ይህ የኢያሚን ልጅ እንዴት ነዋ? እግዚአብሔር አዝዞታልና ተዉት፥ ይርገመኝ። ምናልባት መከራዬን አይቶ ስለ ርግማኑ በዚህ ቀን መልካም ይመልስልኛል” አላቸው። ዳዊትና ሰዎቹም በመንገድ ይሄዱ ነበር፤ ሳሚም በተራራው አጠገብ በአቅራቢያው ይሄድ ነበር፤ ሲሄድም ይረግመው፥ ድንጋይም ይወረውርበት ነበር፤ ትቢያም ይበትንበት ነበር።
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ 16 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ 16:5-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች