መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 14:1-4

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 14:1-4 አማ2000

በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ በዮ​አስ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አስ ልጅ አሜ​ስ​ያስ ነገሠ። መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ ዕድ​ሜው ሃያ አም​ስት ዓመት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ። እና​ቱም ዮአ​ድም የተ​ባ​ለች የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ነበ​ረች። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን አባቱ ኢዮ​አስ እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ እንጂ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት አላ​ደ​ረ​ገም። ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ባሉት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።