መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 13:10-21

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 13:10-21 አማ2000

በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ በሠ​ላሳ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ዮአስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት አል​ራ​ቀም፤ ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ሄደ። የቀ​ረ​ውም የዮ​አስ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ከአ​ሜ​ስ​ያስ ጋር የተ​ዋ​ጋ​በት ኀይሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? ዮአ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በዙ​ፋኑ ላይ ተቀ​መጠ፤ ዮአ​ስም በሰ​ማ​ርያ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት ጋር ተቀ​በረ። ኤል​ሳ​ዕም በሚ​ሞ​ት​በት በሽታ ታመመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለ​ቀ​ሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰረ​ገ​ላ​ቸ​ውና ፈረ​ሰ​ኛ​ቸው” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ቀስ​ት​ህ​ንና ፍላ​ጻ​ዎ​ች​ህን ውሰድ” አለው፤ ቀስ​ቱ​ንና ፍላ​ጻ​ዎ​ቹ​ንም ወሰደ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ንጉሥ አለው፥ “እጅ​ህን በቀ​ስቱ ላይ ጫን።” ዮአ​ስም እጁን በቀ​ስቱ ላይ ጫነ፤ ኤል​ሳ​ዕም እጁን በን​ጉሡ እጅ ላይ ጫነ፦ “የም​ሥ​ራ​ቁ​ንም መስ​ኮት ክፈት” አለ፤ ከፈ​ተ​ውም። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ወር​ውር” አለው፤ ወረ​ወ​ረ​ውም እር​ሱም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒት ፍላጻ ነው፤ ከሶ​ርያ የመ​ዳን ፍላጻ ነው፤ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ ሶር​ያ​ው​ያ​ንን በአ​ፌቅ ትመ​ታ​ለህ” አለ። ኤል​ሳ​ዕም ደግሞ፥ “ፍላ​ጻ​ዎ​ች​ህን ውሰድ” አለው ወሰ​ዳ​ቸ​ውም። የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ንጉሥ፥ “ምድ​ሩን ምታው” አለው። ንጉ​ሡም ሦስት ጊዜ መትቶ ቆመ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው አዝኖ፥ “አም​ስት ወይም ስድ​ስት ጊዜ መት​ተ​ኸው ቢሆን ኖሮ ሶር​ያ​ው​ያ​ንን እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ በመ​ታ​ኻ​ቸው ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ሶር​ያን ትመ​ታ​ለህ” አለ። ኤል​ሳ​ዕም ሞተ፤ ቀበ​ሩ​ትም። ከሞ​ዓ​ብም አደጋ ጣዮች በየ​ዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ ወደ ሀገሩ ይገቡ ነበር። ሰዎ​ችም አንድ ሰው ሲቀ​ብሩ አደጋ ጣዮ​ችን አዩ፤ ሬሳ​ው​ንም በኤ​ል​ሳዕ መቃ​ብር ላይ ጣሉት፤ የኤ​ል​ሳ​ዕ​ንም አጥ​ንት በነካ ጊዜ ሰው​ዬው ድኖ በእ​ግሩ ቆመ።