መጽሐፈ ዕዝራ ካልእ 9
9
1ዕዝራም ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ተነሥቶ ወደ ናሴሩ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኤሊያሲብ” ይላል። ልጅ ወደ ዮሐናን ቤት ሄደ። 2በዚያም ተቀምጦ ስለ ታላላቆችና ብዙዎች ኀጢአቶቻቸው እያለቀሰ እህልን አልበላም፤ ውኃንም አልጠጣም። 3ከዚህ በኋላ ከምርኮ ለተመለሱ ሁሉ በኢየሩሳሌም ይገኙ ዘንድ፥ 4እስከ ሁለትና እስከ ሦስት ቀን ድረስ ያልተገኙና ያልደረሱ ሁሉ እንደ ሥርዐታቸው በአለቆቻቸው ቅጣት ይቀጡ ዘንድ፥ ከብቶቻቸውም ይወረሱ ዘንድ፥ እነርሱም ከወገኖቻቸው ይለዩ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ዐዋጅ ነገረላቸው።
5የይሁዳና የብንያም ወገኖችም በዘጠነኛው ወር በሃያኛው ቀን በሦስት ቀን ውስጥ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። 6ሁሉም በቤተ መቅደሱ አደባባይ ተቀመጡ፤ ክረምት ነበርና ስለ ውርጩ ጽናት ይንቀጠቀጡ ነበር። 7ዕዝራም ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፥ “ከአሕዛብ ወገን ሚስት ያገባችሁ እናንተ በደላችሁ፤ በእስራኤልም ላይ ኀጢአትን ጨመራችሁ። 8አሁንም ለእግዚአብሔር ተናዘዙ፤ የአባቶቻችንንም አምላክ አመስግኑት። 9ፈቃዱንም ፈጽሙ፤ ከምድር አሕዛብና ከባዕዳት ሚስቶቻችሁም ተለዩ።”
10ሁሉም በሙሉ በታላቅ ድምፅ ጮኸው እንዲህ አሉት፥ “እሺ አንተ እንዳዘዝኸን እናደርጋለን። 11ነገር ግን ሰዉ ብዙ ነው፤ ጊዜውም ክረምት ነው፤ ፈጥነንም እናደርገው ዘንድ አንችልም፤ ሥራውም የአንድ ቀን ወይም የሁለት ቀን ሥራ አይደለም፤ በዚህ ፈጽመን በድለናልና። 12አሁንም ከልዩ ወገን ሚስት ያገቡ መሳፍንት ሁሉና መንደረተኞችም ተሰብስበው ይምጡ። 13በዚህ ሥራ ያገኘን የእግዚአብሔር ቍጣ ከእኛ ይርቅ ዘንድ መንደረተኞቻቸውንና ሽማግሌዎቻቸውን፥ አለቆቻቸውንም ይቅጠሯቸው።”
14የአዛሄል ልጅ ዮናታን፥ የታቃኑ ልጅ ኢያዝያስም መጡ፤ ሞሶላሞስ፥ ሌዊ፥ ሳባጢዎስ፥ እነርሱም እንዲህ ተባበሩ። 15ከምርኮ የተመለሱትም ሁሉ እንዲሁ አደረጉ። 16ካህኑ ዕዝራም ካገሮቻቸው ሽማግሌዎች፥ በያገራቸውም ከሚኖሩት ሁሉ ስማቸው ልዩ ልዩ የሆነ ሰዎችን መረጠ፤ እንዲህም ያደርጉ ዘንድ እስከ ዐሥረኛው ወር መባቻ ድረስ ተቃጠሩ። 17ከልዩ ወገን ሚስት ያገቡ እነዚያም ሰዎች ሁሉ “እስከ መጀመሪያው ወር መባቻ እንፈታለን” ብለው ነገራቸውን ጨረሱ።
18ከካህናቱም ውስጥ ከባዕድ ወገን ሚስት ያገቡ ተገኙ። 19እነርሱም የኢዮሴዴቅ ልጅ የኢያሱ ልጆችና ወንድሞቹ፥ ማቴላስ፥ አልዓዛር፥ ዮሬቦስና ዮአዳኖስም ናቸው። 20ሚስቶቻቸውንም ፈትተው ስለ ኀጢአታቸው መሥዋዕት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የበጎች ሙክቶች ይላል። ይሠዉ ዘንድ ጀመሩ። 21ከኤሞርም ልጆች ሐናንያ፥ ዘብዴዎስ፥ ሜኑስ፥ ሴሜዎስ፥ ኢያርማየልና አዛርያ ናቸው። 22ከፌትርኤልም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፌሱር” ይላል። ልጆች ኢልዮኒስ፥ ማስያስ፥ አስማኤሎስ፥ ናትናአሎስ፥ ዎቅዲሎስና አልታሳ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሳሎአስ” ይላል። ናቸው።
23ከሌዋውያንም ወገን ዮዛባዶስ፥ ሳምያስ፥ ቃሊጣስ የሚሉት ቆዮስ፥ ፋትያስ፥ ይሁዳና ዮናስ ናቸው። 24ከመዘምራንም ወገን ኤልያሳቦስና ባካሮስ ናቸው። 25ከበረኞችም ወገን ሴሎምና ጦልባኒስ ናቸው። 26ከእስራኤል ከፎሮስ ልጆች ወገንም ኢየርማስ፥ ኤዝያስ፥ ሚልክያስ፥ ሚያኤሎስ፥ አልዓዛር፥ አስብያስ፥ ባኒያስ ናቸው። 27ከኤላ ልጆች ወገን ማጣንያስ፥ ዘካርያስ፥ ኢያዚሬሎስ፥ አብድዮስ፥ ኢያሬሞትና ኤዲያስ ናቸው። 28ከዛሞትም ልጆች ወገን ኤሊያዳስ፥ ኤሊያሲሞስ፥ ኦቶንያስ፥ ኢያሪሞስ፥ ሳባቶስ፥ ዘራሊያስ ናቸው። 29ከቤባይም ልጆች ወገን ዮሐንስ፥ ሐናንያ፥ ዮዛብዴዎስ፥ አሜቴዎስ ናቸው። 30ከማኒ ልጆችም ወገን ኦላሞስ፥ ማምኮስ፥ ኢያዴዎስ፥ ኢያሶቦስ፥ አስሔሎስ፥ ኢያርሞት ናቸው። 31ከዓዲ ልጆችም ናሐቶስ፥ ሞሐስያስ፥ ለቁናስ፥ ኒዶስ፥ ቢስቀስ-ጰስሚስ ሲአቱል ባልኑስ፥ ሜናስያስ ናቸው፥ 32ከሐናንያ ልጆችም ኢሊዮሳስ፥ አስያስ፥ ሚልክያስ፥ ስብያስ፥ ስምዖን፥ ኮሳሜዎስ ናቸው። 33ከአሶም ልጆችም መልጠኒዎስ፥ መጣቲያስ፥ ሳባኔዎስ፥ ኤሌፍላት፥ ምናሴ፥ ሴሜይ ናቸው። 34ከባኒ ልጆችም ኤርምያስ፥ ሞምዲስ፥ ስማኤል፥ ኢዮኤል፥ መምዲ፥ ጴዴያስ፥ አናስ፥ ቀሪባሶን፥ አናሲቦስ፥ መንጠኒሞስ፥ አልያሲስ፥ በኑስ፥ ኤልያሊ፥ ሰማይስ፥ ሰላምያስ፥ ናታንያስ ናቸው። ከኤዛርያስ ልጆችም ሴሲስ፥ ኤዝርል፥ አዛኤል፥ ሳማጢስ፥ ዘምበሪ፥ ኢዮሶፎስ ናቸው። 35ከነሐማ ልጆችም ማዚጢያስ፥ ዘቢዲያስ፥ ኤዴስ፥ ኢዮኤል፥ በኒያስ ናቸው። 36ከባዕዳን ከአሕዛብ ወገን ሚስት ያገቡት ሰዎች ሁሉ ሚስቶቻችውን ሁሉ ከልጆቻቸው ጋር አስወጧቸው።
37ካህናትና ሌዋውያንም፥ ብዙዎች እስራኤልም በሰባተኛው ወር መባቻ በኢየሩሳሌም በያገራቸው ተቀመጡ፤ የእስራኤልም ልጆች በየአውራጃቸው ተመለሱ። 38በቤተ መቅደሱ በር በምሥራቃዊው አደባባይ ሁሉም በአንድነት ተሰበሰቡ። 39ካህኑንና ጸሓፊዉን ዕዝራንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሰጠውን የሙሴን ሕግ ያመጣ ዘንድ ነገሩት። 40የካህናት አለቃ ዕዝራም በሰባተኛው ወር መባቻ ለሕዝቡ፥ ለወንዶችም፥ ለሴቶችም ለካህናቱም ሁሉ ሕጉን ይሰሙ ዘንድ አነበበላቸው። 41በቤተ መቅደሱም በር ባለው አደባባይ በወንዶቹና በሴቶቹ ፊት ከነግህ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበላቸው፤ ሁሉም በፍጹም ልባቸው ሕጉን አደመጡ። 42ካህኑና የሕጉ ጸሓፊ ዕዝራም ከእንጨት በተሠራ መረባርብ ላይ ቆመ። 43ከእርሱም ጋር፦ መተጢያስን፥ ሳሙስን፥ ሐናንያን፥ አዛርያን፥ ኡርያስን፥ ሕዝቅያስን፥ በአልስሞስንም በቀኙ አቆማቸው። 44በግራውም በኩል ፈሐልዴዎስን፥ ሚሳኤልን፥ ሚልክያስን፥ ሎታሳብስን፥ ናባሪያንና ዘካርያስን አቆመ። 45ዕዝራም ያን መጽሐፍ ይዞ በሕዝቡ ፊት ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ ያከብሩት ነበር። 46የሕጉንም መጽሐፍ በገለጠ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ተነሥተው ቆሙ፤ አዛርያም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዕዝራ” ይላል። ሁሉን የሚገዛ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገነው። 47ሁሉም በሙሉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለሱለት፤ እጆቻቸውንም ወደ ላይ አንሥተው በምድር ወድቀው ለእግዚአብሔር ሰገዱ። 48ሌዋውያኑም ኢያሱ፥ አኑሲ፥ ሰራቢያስ፥ ኢያዲኖስ፥ ኢያቆብስ፥ ሳብጣያስ፥ አውጥያስ፥ ሚሐና፥ ቀሊጦስ፥ አዛርያ፥ ጠዛብዶስ፥ ሐኒያስ፥ ፈልጣስ የእግዚአብሔርን ሕግ አስተማሯቸው። 49ባነበበላቸውም ጊዜ ሁሉም በአንድነት ሆነው ሰሙ። 50አጠራጢም የካህናቱን አለቃና ጸሓፊውን ዕዝራን፥ ለሁሉ የሚያስተምሩ ሌዋውያንንም እንዲህ አላቸው፦ 51“ይቺ ቀን ለእግዚአብሔር የተቀደሰች ናት፥” ሁሉም ሕጉን በሰሙ ጊዜ አለቀሱ። 52እንዲህም ተባባሉ፥ “ሂዱና ምሳችሁን ብሉ፤ ጠጡም፤ ለሌላቸውም ሰዎች ምጽዋትን ላኩ። ይቺ ቀን ለእግዚአብሔር የተቀደሰች ናትና፥ አትዘኑም፤ እግዚአብሔር አይጥላችሁምና።” 53ሌዋውያንም ሕዝቡን ሁሉ እንዲህ ብለው አዘዙ “ይቺ ቀን የተቀደሰች ናትና አትዘኑ።” 54ሁሉም ሊበሉና ሊጠጡ፥ ደስታም ሊያደርጉ፥ ለሌላቸውም ሰዎች ምጽዋትን ሊሰጡ ሄዱ። 55በተሰበሰቡበት ቦታም ያስተማሯቸውን ቃል በሰሙ ጊዜ ታላቅ ደስታን አደረጉ።#በዕዝራ ቀዳማዊና በዕዝራ ካልእ ውስጥ ያለው ታሪክ አንድ ሲሆን በስሞች አጠራር ልዩነት አለ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዕዝራ ካልእ 9: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ