መጽሐፈ ዕዝራ ካልእ 7
7
የቤተ መቅደሱ ቅዳሴ
1ከዚህም በኋላ የቄሌ-ሶርያና የፊንቂስ ገዥ ሲሳኒስና፥ ሳትራቡዛኒስ፥ ባልንጀሮቻቸውም ንጉሡ ዳርዮስ እንዳዘዘ ይሠሩ ዘንድ ጀመሩ። 2እነርሱም ተግተው ከአይሁድ ሽማግሌዎች ጋር ቆመው ያዝዙ ነበር።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የአይሁድ ሽማግሌዎችንና የቤተ መቅደሱን አለቆች እየረዱ የተቀደሰውን ሥራ ይቈጣጠሩ ነበር” ይላል። 3የቤተ መቅደሱም ሥራ፥ ነቢያቱ ሐጌና ዘካርያስ ትንቢት እየተናገሩላቸው ፈጥኖ ተከናወነ። 4በፋርስ ነገሥታት በቂሮስና ዳርዮስ፥ በአርጤክስስም ፈቃድ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሥራውን ፈጸሙ። 5ቤተ መቅደሱ አዳር በሚባል ወር በጨረቃ በስምንተኛው ቀን በዳርዮስ በስድስተኛው ዓመተ መንግሥት ተፈጸመ። 6የእስራኤል ልጆችና ካህናት፥ ሌዋውያንም፥ ከምርኮ የተመለሱት ሕዝቡም ሁሉ በሙሴ መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ሥርዐቱን አደረጉ። 7ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዳሴም ቤት መቶ ኮርማዎችን፥ ሁለት መቶ ፍየሎችና አራት መቶ በጎችን አቀረቡ። 8ስለ እስራኤልም ኀጢአት ሁሉ ማስተስረያ፦ ባሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ሹሞች ቍጥር ዐሥራ ሁለት ሙክቶችን አቀረቡ። 9ካህናቱና ሌዋውያኑም በሙሴ መጽሐፍ እንደ ተጻፈ እንደ ሥርዐታቸው ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር አገልግሎት በየወገናቸው ልብሰ ተክህኖውን ለብሰው ቆሙ። በረኞችም በየበሮቻቸው ቆሙ።
የፋሲካ በዓል
10ከምርኮ የተመለሱ የእስራኤል ልጆችም በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል አከበሩ። ካህናቱና ሌዋውያኑ፥ ሁሉም ራሳቸውን በአንድነት አንጽተዋልና። 11ከምርኮ የተመለሱት ልጆቻቸው ግን ሁሉም ሰውነታቸውን አላነጹም ነበር፤ ሌዋውያን ግን ሁሉም ነጽተው ነበርና፤ 12ከምርኮ ለተመለሱት ለእስራኤል ልጆች ለወንድሞቻቸው ለካህናትና ለራሳቸውም የፋሲካን በግ ሠዉ። 13ከምርኮ የተመለሱ የእስራኤል ልጆች ሁሉ፥ እግዚአብሔርንም ይሹት ዘንድ ከምድር አሕዛብ ርኵሰት የተለዩት ሁሉ ፋሲካውን በሉ። 14በእግዚአብሔርም ፊት ደስ ብሏቸው ሰባት ቀን የቂጣዉን በዓል አከበሩ። 15እግዚአብሔር የፋርሱን ንጉሥ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የአሶር ንጉሥ” ይላል። ልቡና መልሶላችዋልና፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ሥራም እጃቸውን አጽንቶላቸዋልና።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዕዝራ ካልእ 7: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ