ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 5:8-11

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 5:8-11 አማ2000

ታም​ነ​ናል፤ ይል​ቁ​ንም ከሥ​ጋ​ችን ተለ​ይ​ተን ወደ ጌታ​ችን እን​ሄ​ዳ​ለ​ንና ደስ ይለ​ናል። አሁ​ንም ብን​ኖ​ርም፥ ብን​ሞ​ትም እር​ሱን ደስ ለማ​ሰ​ኘት እን​ጥ​ራ​ለን። መል​ካም ቢሆን፥ ክፉም ቢሆን በሥ​ጋ​ችን እንደ ሠራ​ነው ዋጋ​ች​ንን እን​ቀ​በል ዘንድ፥ ሁላ​ችን በክ​ር​ስ​ቶስ የፍ​ርድ ዙፋን ፊት እን​ቆ​ማ​ለ​ንና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ዐው​ቀን ሰዎ​ችን እና​ሳ​ም​ና​ለን፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እኛ የተ​ገ​ለ​ጥን ነን፤ እን​ዲ​ሁም በል​ቡ​ና​ችሁ የተ​ገ​ለ​ጥን እንደ ሆን እን​ታ​መ​ና​ለን።