ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 4:1-4

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 4:1-4 አማ2000

ስለ​ዚህ እንደ ቸር​ነቱ የሰ​ጠን ይህ መል​እ​ክት አለ​ንና አን​ሰ​ለ​ችም። ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና። ወን​ጌ​ላ​ችን የተ​ሰ​ወረ ቢሆ​ንም እንኳ፥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ባ​ቸው ለሚ​ጠ​ፉት ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው የክ​ር​ስ​ቶስ የክ​ብሩ ወን​ጌል ብር​ሃን እን​ዳ​ያ​በ​ራ​ላ​ቸው የዚህ ዓለም አም​ላክ ልባ​ቸ​ውን አሳ​ው​ሮ​አ​ልና።