ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 12:2-4

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 12:2-4 አማ2000

በክ​ር​ስ​ቶስ ያመነ አንድ ሰው አው​ቃ​ለሁ፤ ዘመኑ ከዐ​ሥራ አራት ዓመት በፊት ነው፤ ነገር ግን በሥ​ጋው ይሁን በነ​ፍሱ እንጃ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል፤ ያን ሰው እስከ ሦስ​ተ​ኛው ሰማይ ድረስ ነጥ​ቀው ወሰ​ዱት። ያን ሰው አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ በሥ​ጋው ይሁን በነ​ፍሱ እንጃ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል። ወደ ገነ​ትም ነጥ​ቀው ወሰ​ዱት፤ በዚ​ያም ሰው ሊና​ገ​ረው የማ​ይ​ች​ለ​ውን የማ​ይ​ተ​ረ​ጐም ነገር ሰማ።