መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 3

3
ሰሎ​ሞን ቤተ መቅ​ደስ እንደ ሠራ
(1ነገ. 6፥1-38)
1ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባቱ ለዳ​ዊት በተ​ገ​ለ​ጠ​በት በአ​ሞ​ሪያ ተራራ ዳዊት ባዘ​ጋ​ጀው ስፍራ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመረ። 2በነ​ገ​ሠም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር መሥ​ራት ጀመረ። 3ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠራ ዘንድ የጣ​ለው መሠ​ረት ይህ ነው፤ ርዝ​መ​ቱም በዱ​ሮው ስፍር ስድሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ ነበረ። 4በቤ​ቱም ፊት የነ​በ​ረው ወለል ርዝ​መቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስ​ጡ​ንም በጥሩ ወርቅ ለበ​ጠው። 5ታላ​ቁ​ንም ቤት በዝ​ግባ እን​ጨት ከደ​ነው፤ በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው፤ የዘ​ን​ባ​ባና የሰ​ን​ሰ​ለት አም​ሳ​ልም ቀረ​ጸ​በት። 6ቤቱ​ንም በከ​በ​ረና በተ​መ​ረጠ ዕንቍ፥ በወ​ር​ቅም አስ​ጌ​ጠው፤ ወር​ቁም የፋ​ሩ​ሔም ወርቅ ነበረ። 7ቤቱ​ንም፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም፥ መድ​ረ​ኮ​ቹ​ንም፥ ግን​ቦ​ቹ​ንም፥ ደጆ​ቹ​ንም በወ​ርቅ ለበጠ፤ በግ​ን​ቦ​ቹም ላይ ኪሩ​ቤ​ልን ቀረጸ።
8ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑ​ንም ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ ስድ​ስት መቶ መክ​ሊት በሚ​ያ​ህል በጥሩ ወር​ቅም ኪሩ​ቤ​ልን#“ኪሩ​ቤ​ልን” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ለበ​ጣ​ቸው። 9የም​ስ​ማ​ሮ​ቹም ሚዛን ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አምሳ ሰቅል ወርቅ ነበረ። የደ​ር​ቡ​ንም ጓዳ​ዎች በወ​ርቅ ለበጠ።
10በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ንም ውስጥ ከእ​ን​ጨት ሥራ ሁለ​ቱን ኪሩ​ቤል ሠራ፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው። 11የኪ​ሩ​ቤ​ልም ክን​ፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ የአ​ንዱ የኪ​ሩብ ክንፍ ርዝ​መት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የቤ​ቱ​ንም ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ክንፍ ርዝ​መት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። 12የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ኪሩብ አንዱ ክንፍ አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የቤ​ቱ​ንም ግንብ ይነካ ነበር፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ክንፍ አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የሌ​ላ​ው​ንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። 13የእ​ነ​ዚ​ህም ኪሩ​ቤል ክን​ፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም ቆመው ነበር፤ ፊቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይመ​ለ​ከቱ ነበር።
14ከሰ​ማ​ያ​ዊ​ውም፥ ከሐ​ም​ራ​ዊ​ውም፥ ከቀ​ዩም ሐር፥ ከጥ​ሩም በፍታ መጋ​ረ​ጃ​ውን ሠራ፤ ኪሩ​ቤ​ል​ንም ጠለ​ፈ​በት።
15በቤ​ቱም ፊት ቁመ​ታ​ቸው ሠላሳ አም​ስት ክንድ የነ​በ​ረ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች ሠራ፤ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም ላይ የነ​በ​ረው ጕል​ላት አም​ስት ክንድ ነበረ።
16እንደ ድሪ ያሉ ሰን​ሰ​ለ​ቶ​ች​ንም ሠርቶ በአ​ዕ​ማዱ ራስ ላይ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ መቶም ሮማ​ኖች ሠርቶ በሰ​ን​ሰ​ለቱ ላይ አደ​ረ​ጋ​ቸው። 17አዕ​ማ​ዶ​ቹ​ንም አን​ደ​ኛ​ውን በቀኝ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ፊት አቆ​ማ​ቸው፤ በቀ​ኝም የነ​በ​ረ​ውን ስም ርትዕ#ዕብ. “ያቁም” ይላል። በግ​ራም የነ​በ​ረ​ውን ስም ጽንዕ#ዕብ. “በለዝ” ይላል። ብሎ ጠራ​ቸው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ