መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 16
16
ይሁዳና እስራኤል እንደ ተዋጉ
(1ነገ. 15፥17-22)
1አሳ በነገሠ በሠላሳ ስድስተኛው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ስምንተኛው” ይላል። ዓመት የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ ዘመተ፥ ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ አሳ ማንም መውጣትና መግባት እንዳይችል ራማን ሠራት። 2አሳም ከእግዚአብሔር ቤትና ከንጉሥ ቤት መዝገብ ብርና ወርቅ ወስዶ፦ በደማስቆ ወደ ተቀመጠው ወደ ሶርያ ንጉሥ ወደ ወልደ አዴር ላከ። እንዲህም አለው፦ 3“በአባቴና በአባትህ መካከል እንደ ነበረው ቃል ኪዳን በእኔና በአንተ መካከል አድርግ፤ የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ከእኔ ዘንድ እንዲርቅ መጥተህ ትወጋው ዘንድ እነሆ፥ ወርቅና ብር ልኬልሃለሁ።” 4ወልደ አዴርም ንጉሡን አሳን ሰማው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰደደ፤ እነርሱም አእዮንንና ዳንን፥ አቤልማይምንና የንፍታሌምንም አውራጃ ከተሞች ሁሉ መቱ። 5ባኦስም በሰማ ጊዜ ራማን መሥራት ተወ፤ ሥራውንም አቋረጠ። 6የይሁዳ ንጉሥ አሳም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ ባኦስ ይሠራበት የነበረውን የራማን ድንጋይና እንጨት ወሰደ፤ እርሱም ገባዖንንና መሴፋን ሠራበት።
7በዚያን ጊዜም ነቢዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እንዲህ አለው፥ “በሶርያ ንጉሥ ታምነሃልና፥ በአምላክህም በእግዚአብሔር አልታመንህምና ስለዚህ የሶርያ ንጉሥ ጭፍራ ከእጆችህ አምልጠዋል። 8ኢትዮጵያውያንና የልብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሩአቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አልነበሩምን? በእግዚአብሔር ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጣቸው። 9እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።” 10አሳም በነቢዩ በአናኒ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በግዞት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አስጨነቀ።
11የአሳም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል። 12አሳም በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት እግሩን ታመመ፤ ደዌውም ጸናበት፤ ነገር ግን በሕማሙ ጊዜ ባለ መድኀኒቶችን እንጂ እግዚአብሔርን አልፈለገም። 13አሳም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በነገሠም በአርባ አንደኛው ዓመት ሞተ። 14ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቱ በተሞላ አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የቀብር ሥርዐት አደረጉለት።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 16: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ