መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 21:3-6

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 21:3-6 አማ2000

አሁ​ንም አም​ስት እን​ጀራ በእ​ጅህ ካለ፥ ወይም በእ​ጅህ ያለ​ውን ስጠኝ” አለው። ካህ​ኑም ለዳ​ዊት መልሶ፥ “ሁሉ የሚ​በ​ላው እን​ጀራ የለ​ኝም፤ ነገር ግን የተ​ቀ​ደሰ እን​ጀራ አለ፤ ብላ​ቴ​ኖቹ ከሴ​ቶች ንጹ​ሓን እንደ ሆኑ መብ​ላት ይች​ላሉ” አለው። ዳዊ​ትም ለካ​ህኑ መልሶ፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተን ወደ መን​ገድ ከወ​ጣን ዛሬ ሦስ​ተኛ ቀና​ችን ነው። እኔም ብላ​ቴ​ኖ​ቼም ንጹ​ሓን ነን። ነገር ግን ዛሬ ሰው​ነቴ ንጽ​ሕት ስለ ሆነች ነው እንጂ ይህች መን​ገድ የነ​ጻች አይ​ደ​ለ​ችም” አለው። ካህኑ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእ​ርሱ ፋንታ ትኩስ እን​ጀራ ይደ​ረግ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከአ​ለው ኅብ​ስት በቀር ሌላ እን​ጀራ አል​ነ​በ​ረ​ምና የቍ​ር​ባ​ኑን ኅብ​ስት ሰጠው።