መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 7
7
ሰሎሞን ቤተ መንግሥቱን እንደ ሠራ
1ሰሎሞንም የራሱን ቤት በዐሥራ ሦስት ዓመት ሠራ፤ የቤቱንም ሥራ ሁሉ ጨረሰ። 2የሊባኖስ ዱር ቤት የሚባል ቤትንም ሠራ፤ ርዝመቱንም መቶ ክንድ፥ ስፋቱንም አምሳ ክንድ፥ ቁመቱንም ሠላሳ ክንድ አደረገ፤ የዋንዛም እንጨት በሦስት ወገን በተሠሩ አዕማድ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአዕማዱም ላይ የዋንዛ እንጨት አግዳሚ ሰረገሎች ነበሩ። 3በአዕማዱም ላይ በነበሩ አግዳሚዎች ቤቱ በዋንዛ ሳንቃ ተሸፍኖ ነበር፤ አዕማዱም በአንዱ ወገን ዐሥራ አምስት፥ በአንዱ ወገን ዐሥራ አምስት የሆኑ አርባ አምስት ነበሩ። 4መስኮቶቹም በሦስት ወገን ነበሩ፤ መስኮቶቹም በሦስት ወገን ፊት ለፊት ይተያዩ ነበር። 5ደጆቹ፥ መቃኖቹና የታችኛውና የላይኛው መድረኮች ሁሉ አራት ማዕዘን ነበሩ፤ መስኮቶቹም በሦስት ወገን ሆነው ፊት ለፊት ይተያዩ ነበር። 6አዕማዱም ያሉበትን ቤት ሠራ፤ ርዝመቱም አምሳ ክንድ፥ ስፋቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ፤ በእርሱም ፊት ደግሞ ታላቅ አዕማድና መድረክ ያሉበት ወለል ነበረ። 7የሚፈርድበትም የቤቱ ዙፋን በዚያ አለ። ለመፍረጃውም ቤትን ሠራ፤ ከላይ እስከ ታችም በዋንዛ እንጨት አያያዘው። 8ከፍርድ ሰቀላ ወደ ውስጥ፥ በሌላውም አደባባይ ውስጥ የነበረውን የሚኖርበትን ቤት እንዲሁ ሠራ፤ እንደዚህም ቤት ያለ ቤትን ሰሎሞን ላገባት ለፈርዖን ልጅ ሠራ።
9ይህም ሁሉ ከመሠረቱ ጀምሮ እስከ ጕልላቱ ድረስ በከበረና በተጠረበ በውስጥና በውጭ በልክ በተከረከመ ድንጋይ ተሠርቶ ነበር፤ በውጭውም እስከ ታላቁ አደባባይ ድረስ እንዲሁ ነበረ። 10መሠረቱም ዐሥር ዐሥር ክንድና ስምንት ስምንት ክንድ በሆኑ በከበሩ በታላላቅ ድንጋዮች ተሠርቶ ነበር። 11በላዩም ልክ ሆኖ የተከረከመ ጥሩ ድንጋይና የዝግባ ሣንቃ ነበረ። 12በታላቁም አደባባይ ዙሪያ የነበረው ቅጥር እንደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ውስጠኛው አደባባይ ቅጥርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ወገን በተጠረበ ድንጋይ አንዱም ወገን በዝግባ ሳንቃ ተሠርቶ ነበር።
13ንጉሡም ሰሎሞን ልኮ ኪራምን ከጢሮስ አስመጣ። 14እርሱም ከንፍታሌም ወገን የነበረች የባል አልባ ሴት ልጅ ነበረ፤ አባቱም የጢሮስ ሰው ናስ ሠራተኛ ነበረ፤ የናስንም ሥራ ሁሉ ይሠራ ዘንድ በጥበብና በማስተዋል፥ በብልሃትም ተሞልቶ ነበር። ወደ ንጉሡም ወደ ሰሎሞን መጥቶ ሥራውን ሁሉ ሠራ። 15በቤቱ ውስጥ ላለው ወለል ሁለቱን የናስ አዕማድ ሠራ፤ የአንዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፤ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዓምዱም ውፍረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍትም ነበረ። ሁለተኛውም ዓምድ እንዲሁ ነበረ። 16በሁለቱም አዕማድ ራስ ላይ እንዲቀመጡ ከፈሰሰ ናስ ሁለት ጕልላትን ሠራ፤ የአንዱም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ፥ የሁለተኛውም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ። 17በአዕማዱም ራስ ላይ የነበሩትን ጕልላቶች ይሸፍኑ ዘንድ ሁለት እንደ መርበብ ሥራ አደረገ፤ አንዱም መርበብ ለአንዱ ጕልላት፥ ሁለተኛውም መርበብ ለሁለተኛው ጕልላት ነበረ። 18ሮማኖችንም ሠራ፤ በአንድ ጕልላት ዙሪያ በሁለት ተራ፥ በአንድም መርበብ ላይ ሁለት ተራ ነበረ፤ እንዲሁም ለሁለተኛው ጕልላት አደረገ። 19በወለሉም አዕማድ በነበሩት ጕልላቶች ላይ የሱፍ አበባ የሚመስል ሥራ አራት ክንድ አድርጎ ቀረጸ። 20በሁለቱም አዕማድ በነበሩት ጕልላቶች ላይ በመርበቡ ሥራ አጠገብ ሮማኖቹን አደረገ። ሮማኖቹም በአንዱ ወገን ሁለት መቶ ነበሩ። የሁለተኛውም ጕልላት እንዲሁ ነበረ። 21አዕማዱንም በመቅደሱ ወለል አጠገብ አቆማቸው፤ የቀኙንም ዓምድ አቁሞ ያቁም ብሎ ጠራው፤ የግራውንም ዓምድ አቁሞ በለዝ ብሎ ጠራው። 22በአዕማዱም ራስ ላይ የሱፍ አበባ የሚመስል ሥራ አደረገ። እንዲሁም የአዕማዱ ሥራ ተጨረሰ።
23ከፈሰሰም ናስ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፥ ቁመቱም አምስት ክንድ፥ በዙሪያውም ሠላሳ ክንድ የሆነ ክብ ኩሬ ሠራ። 24ከከንፈሩም በታች ለአንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአንድ ክንድም ዐሥር ጕብጕቦች አዞረበት፤ ከንፈሮቹም እንደ ጽዋ ከንፈር ነበሩ። በውስጡም አበቦች በቅለውበት ነበር። ውፍረቱም ስንዝር ነበር። 25ኩሬውም በዐሥራ ሁለት በሬዎች ምስል ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ከእነርሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱም ወደ ምዕራብ፥ ሦስቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስቱም ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር። ኩሬውም በላያቸው ነበረ፤ የሁሉም ጀርባቸው በስተውስጥ ነበረ። 26ውፍረቱም አንድ ጋት ነበረ። ከንፈሩም እንደ ጽዋ ከንፈር ተሠርቶ ነበር፤ እንደ ሱፍ አበባዎች ሆኖ ተከርክሞ ነበር። ሁለት ሺህም የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር። 27ዐሥርም የናስ መቀመጫዎችን ሠራ፤ የአንዱም መቀመጫ ርዝመት አራት ክንድ፥ ወርዱም አራት ክንድ፥ ቁመቱም ሦስት ክንድ ነበረ። 28መቀመጫዎችንም እንዲሁ ሠራ፤ እርስ በርሳቸውም አያይዞ ሰንበር ባለው ክፈፍ ሠራቸው። 29በክፈፎቹም መካከል በነበሩ ሰንበሮች ላይ አንበሳዎችና በሬዎች፥ ኪሩቤልም ነበሩ፤ እንዲሁም በክፈፎቹ ላይ ነበረ፤ ከአንበሳዎቹና ከበሬዎቹ በታች ሻኩራ የሚመስል ተንጠልጥሎ ነበር። 30በየመቀመጫዎቹም ሁሉ አራት የናስ መንኰራኵሮች ነበሩባቸው፤ መንኰራኵሮቹም የሚዞሩበትን የናስ ወስከምት ሠራ፤ ከመታጠቢያውም ሰን በታች በአራቱ ማዕዘን በኩል አራት በምስል የፈሰሱ እግሮች ነበሩ። 31በክፈፉም ውስጥ የነበረ አንገት አንድ ክንድ ነበረ፤ አንገቱም ድቡልቡል ነበረ፤ ቁመቱም ክንድ ተኩል ነበረ። በአንገቱም ላይ ቅርጽ ነበረበት፤ ክፈፉ ግን አራት ማዕዘን ነበረ እንጂ ድቡልቡል አልነበረም። 32አራቱም መንኰራኵሮች ከሰንበሮቹ በታች ነበሩ፤ የመንኰራኵሮቹም ወስከምት በመቀመጫው ውስጥ ነበረ፤ የመንኰራኵሩም ቁመት ክንድ ተኩል ነበረ። 33የመንኰራኵሮቹም ሥራ እንደ ሰረገላ መንኰራኵር ሥራ ነበረ፤ ወስከምቶቹና የመንኰራኵሮቹ ክፈፍ፥ ቅትርቶቹም፥ ወስከምቱ የሚገባበት ቧምቧ ሁሉ በምስል የፈሰሰ ነበር። 34በየአንዳንዱም መቀመጫ በአራቱ ማዕዘን በኩል አራት ደገፋዎች ነበሩ፤ ደገፋዎቹም ከመቀመጫው ጋር ተጋጥመው ነበር። 35በመቀመጫውም ራስ ላይ ስንዝር የሚሆን ድቡልቡል ነገር ነበረ፤ በመቀመጫውም ላይ የነበሩ መያዣዎችና ሰንበሮች ከእርሱ ጋር ይጋጠሙ ነበረ፤ ከላይም ክፍት ነበረ፤ 36በክፈፎቻቸውም ኪሩቤልና አንበሶች የዘንባባ ዛፎችም ነበሩ፤ እያንዳንዱም ፊት ለፊት በስተውስጥና በዙሪያው ተያይዞ ነበር። 37እንዲሁም ዐሥሩን መቀመጫዎች ሠራ፤ ሁሉም በመጠን፥ በንድፍም ትክክሎች ነበሩ።
38ዐሥሩንም የናስ መታጠቢያ ሰን ሠራ፤ አንዱ መታጠቢያ ሰን አርባ የባዶስ መስፈሪያ ያነሣ ነበር፤ እያንዳንዱም መታጠቢያ ሰን አራት ክንድ ነበረ፤ በዐሥሩም መቀመጫዎች ላይ በእያንዳንዱ አንድ አንድ መታጠቢያ ሰን ይቀመጥ ነበር። 39አምስቱንም መቀመጫዎች በቤቱ ቀኝ፥ አምስቱንም በቤቱ ግራ አኖራቸው፤ ኩሬውንም በቤቱ ቀኝ በአዜብ ፊት ለፊት በስተምሥራቅ አኖረው።
ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት መገልገያ ዕቃዎችን እንደ ሠራ
(2ዜ.መ. 4፥11፤ 5፥1)
40ኪራምም ምንቸቶችንና መጫሪያዎችን፥ ድስቶችንም ሠራ፤ ኪራምም ለንጉሡ ለሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ። 41ሁለቱንም አዕማድ፥ በሁለቱም አዕማድ ራስ ላይ የነበሩትን ኩብ የሚመስሉትን ጕልላቶች፥ በሁለቱም አዕማድ ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጕልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መርበቦች፥ 42በሁለቱም አዕማድ ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጕልላቶች ይሸፍኑ ዘንድ ለእያንዳንዱ መርበብ በሁለት በሁለት ተራ አድርጎ ለሁለቱ መርበቦች አራት መቶ ሮማኖችን አደረገ። 43ዐሥሩንም መቀመጫዎች፥ በመቀመጫዎቹም ላይ የሚቀመጡትን ዐሥሩን መታጠቢያ ሰን፥ 44አንዱንም ኩሬ፥ ከኩሬውም በታች የሚሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን በሬዎች፥ 45ምንቸቶቹንም፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ዕቃዎቹንም ሁሉ ኪራም ለንጉሡ ለሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት ሠራ። በንጉሡ ቤትና በእግዚአብሔር ቤትም አርባ ስምንት አዕማድ ነበሩ። ኪራምም ለንጉሡ የሠራቸው ዕቃዎች ሁሉ ከጥሩ ናስ ነበር። 46በዮርዳኖስም ሜዳ በሱኮትና በተርታን መካከል ባለው በወፍራሙ መሬት ውስጥ አስፈሰሰው። 47ይህ ሁሉ ሥራ ለተሠራበት ናስ ሚዛን አልነበረውም፤ የናሱም ሚዛን ብዙ ነበርና አይቈጠርም ነበር።
48ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ቤት ዕቃን ሁሉ አሠራ፤ የወርቁን መሠዊያ፥ የገጹም ኅብስት የነበረበትን የወርቅ ገበታ፥ 49በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት አምስቱ በቀኝ፥ አምስቱም በግራ የሚቀመጡትን ከጥሩ ወርቅ የተሠሩትንም መቅረዞች፥ የወርቁንም አበባዎችና ቀንዲሎች፥ መኮስተሪያዎችንም፥ 50ከጥሩ ወርቅም የተሠሩትን ጽዋዎችና ጕጠቶች፥ ድስቶቹንና ጭልፋዎቹንም፥ ማንደጃዎቹንም፥ ጽንሐሖችን፥ ለውስጠኛውም ቤት ለቅድስተ ቅዱሳን ደጆች፥ ለቤተ መቅደሱም ደጆች የሚሆኑትን የወርቅ ማጠፊያዎች አሠራ።
51እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት የአሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን፥ ራሱም የቀደሰውን፥ የብርና የወርቅ ዕቃ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 7: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ