መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 27

27
1የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችና የሺህ አለ​ቆች፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም ለን​ጉ​ሡና ለን​ጉሡ ትእ​ዛዝ ሁሉ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ሹማ​ምት እንደ ቍጥ​ራ​ቸው በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ። እነ​ዚ​ህም ክፍ​ሎች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓ​መቱ ወራት ሁሉ በየ​ወሩ ይገ​ቡና ይወጡ ነበር። 2ለመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በአ​ን​ደ​ኛው ክፍል ላይ የዘ​ብ​ድ​ኤል ልጅ ያሶ​ብ​አም ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። 3እር​ሱም ከፋ​ሬስ ልጆች ነበረ፤ ለመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ ላይ ተሾሞ ነበር። 4በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር ክፍል ላይ የኤቲ ልጅ ዶድያ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሚኮ​ሎት አለቃ ነበር፤#“በእ​ርሱ ክፍል ሚኮ​ሎት አለቃ ነበረ” በዕብ. እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። 5በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር ሦስ​ተ​ኛው የጭ​ፍራ አለቃ የካ​ህኑ የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሽህ ጭፍራ ነበረ። 6ይህ በና​ያስ ከሠ​ላ​ሳው መካ​ከል ኀያል ሆኖ በሠ​ላ​ሳው ላይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ልጁ ዓሚ​ዛ​ባድ ነበረ። 7በአ​ራ​ተ​ኛው ወር አራ​ተ​ኛው አለቃ የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አሳ​ሄል ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ ልጁ ዝባ​ድ​ያና ወን​ድ​ሞቹ ነበሩ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። 8በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር አም​ስ​ተ​ኛው አለቃ ይዝ​ራ​ዊው ሰማ​ኦት ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። 9በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወር ስድ​ስ​ተ​ኛው አለቃ የቴ​ቁ​ሓ​ዊው የአ​ቂስ ልጅ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። 10በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ሰባ​ተ​ኛው አለቃ ከኤ​ፍ​ሬም ልጆች የሆነ ፍሎ​ሳ​ዊው ከሊስ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። 11በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ስም​ን​ተ​ኛው አለቃ ከዛ​ራ​ው​ያን የነ​በ​ረው ኩሳ​ታ​ዊው ሲቦ​ካይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። 12በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር ዘጠ​ነ​ኛው አለቃ ከብ​ን​ያ​ማ​ው​ያን የነ​በ​ረው ዓና​ቶ​ታ​ዊው አቢ​ዔ​ዜር ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። 13በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ዐሥ​ረ​ኛው አለቃ ከዛ​ራ​ው​ያን የነ​በ​ረው ነጦ​ፋ​ዊው መዐ​ርኢ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። 14በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ወር ዐሥራ አን​ደ​ኛው አለቃ ከኤ​ፍ​ሬም ልጆች የነ​በ​ረው ፍር​ዓ​ቶ​ና​ዊው በና​ያስ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። 15በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ዐሥራ ሁለ​ተ​ኛው አለቃ ከጎ​ቶ​ን​ያል ወገን የነ​በ​ረው ነጦ​ፋ​ታ​ዊው ኬል​ዳይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
16በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች ላይ እነ​ዚህ ነበሩ፦ በሮ​ቤ​ላ​ው​ያን ላይ የዝ​ክሪ ልጅ ኤል​ያ​ዛር አለቃ ነበረ፤ በስ​ም​ዖ​ና​ው​ያን ልጅ የመ​ዓካ ልጅ ሰፋ​ጥ​ያስ ነበረ፤ 17በሌዊ ወገን ላይ የቀ​ሙ​ኤል ልጅ አሰ​ብያ፤ በአ​ሮን ወገን ላይ ሳዶቅ፤ 18በይ​ሁዳ ወገን ላይ ከዳ​ዊት ወን​ድ​ሞች ኤል​ያብ፤ በይ​ሳ​ኮር ወገን ላይ የሚ​ካ​ኤል ልጅ ዖምሪ፤ 19በዛ​ብ​ሎን ወገን ላይ የአ​ብ​ድዩ ልጅ ሶማ​ዒ​ያስ፤ በን​ፍ​ታ​ሌም ወገን ላይ የዖ​ዜ​ሄል ልጅ ኢያ​ሪ​ሙት፤ 20በኤ​ፍ​ሬም ልጆች ላይ የአ​ዛ​ዝያ ልጅ ሆሴዕ፤ በም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ላይ የፈ​ዳያ ልጅ ኢዩ​ኤል፤ 21በገ​ለ​ዓድ ምድር ባለው በም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ላይ የዘ​ብ​ድ​ያስ ልጅ ኢዮ​ዳኢ፤ በብ​ን​ያ​ምም ልጆች ላይ የአ​በ​ኔር ልጅ አሳ​ሄል፤ 22በዳን ወገ​ንም ላይ የኢ​ዮ​ራም ልጅ ዓዛ​ር​ኤል፤ እነ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች አለ​ቆች ነበሩ። 23ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝቡ እስ​ራ​ኤ​ልን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት ያበዛ ዘንድ ተና​ግሮ ነበ​ርና ዳዊት ከሃያ ዓመት በታች የነ​በ​ሩ​ትን አል​ቈ​ጠ​ረም። 24የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም መቍ​ጠር ጀመረ፤ ነገር ግን አል​ፈ​ጸ​መም፤ ስለ​ዚህ ነገር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቍጣ ሆነ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በን​ጉሡ በዳ​ዊት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ አል​ተ​ጻ​ፈም።
25በን​ጉ​ሡም ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ የዓ​ዳ​ኤል ልጅ ዓዝ​ሞት ሹም ነበረ፤ በሜ​ዳ​ውም፥ በከ​ተ​ሞ​ቹም፥ በመ​ን​ደ​ሮ​ቹም፥ በግ​ን​ቦ​ቹም ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ የዖ​ዝያ ልጅ ዮና​ታን ሹም ነበረ፤ 26መሬ​ቱን በሚ​ያ​በ​ጃ​ጁ​ትና እር​ሻ​ውን በሚ​ያ​ር​ሱት ላይ የክ​ሉብ ልጅ ዔዝሪ ሹም ነበረ፤ 27በወ​ይ​ንም ቦታ​ዎች ላይ ራማ​ታ​ዊው ሰሜኢ ሹም ነበረ፤ ለወ​ይ​ንም ጠጅ ዕቃ ቤት በሚ​ሆ​ነው በወ​ይኑ ሰብል ላይ የሳ​ፍ​ኒው ዘብዲ ሹም ነበረ። 28በቈ​ላ​ውም ውስጥ ባሉት በወ​ይ​ራ​ውና በሾ​ላው ዛፎች ላይ ጌድ​ራ​ዊው በአ​ል​ሐ​ናን ሹም ነበረ፤ በዘ​ይ​ቱም ቤቶች ላይ ኢዮ​አስ ሹም ነበረ፤ 29በሳ​ሮ​ንም በሚ​ሰ​ማሩ ከብ​ቶች ላይ ሳሮ​ና​ዊው ሰጥ​ራይ ሹም ነበረ፤ በሸ​ለ​ቆ​ዎ​ቹም ውስጥ በነ​በ​ሩት ከብ​ቶች ላይ የዓ​ድ​ላይ ልጅ ሳፋጥ ሹም ነበረ፤ 30በግ​መ​ሎ​ቹም ላይ እስ​ማ​ኤ​ላ​ዊው ኤቢ​ያስ ሹም ነበረ፤ በአ​ህ​ዮ​ቹም ላይ ሜሮ​ኖ​ታ​ዊው ኢያ​ድስ ሹም ነበረ፤ 31በበ​ጎ​ችም ላይ አጋ​ራ​ዊው ያዚዝ ሹም ነበረ። እነ​ዚህ ሁሉ በን​ጉሡ በዳ​ዊት ሀብት ላይ ሹሞች ነበሩ።
32አስ​ተ​ዋ​ይና ጸሓፊ የነ​በ​ረው በአ​ባቱ በኩል የዳ​ዊት አጎት ዮና​ታን አማ​ካሪ ነበረ፤ የአ​ክ​ማ​ኔም ልጅ ኢያ​ሔ​ኤል ከን​ጉሡ ልጆች ጋር ነበረ፤ 33አኪ​ጦ​ፌ​ልም የን​ጉሡ አማ​ካሪ ነበረ። አር​ካ​ዊው ኩሲም የን​ጉሡ አን​ደኛ ወዳጅ ነበረ፤ 34ከአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልም ቀጥሎ የበ​ና​ያስ ልጅ ዮዳ​ሔና አብ​ያ​ታር ነበሩ፤ ኢዮ​አ​ብም የን​ጉሡ ሠራ​ዊት አለቃ ነበረ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ