መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 25
25
የቤተ መቅደስ መዘምራን
1ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶትምም ልጆች በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም የሚዘምሩ ሰዎችን ለማገልገል ለዩ፤ በየአገልግሎታቸውም ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ። 2ከአሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ናታንያ፥ ኤራኤል፤ እነዚህ የአሳፍ ልጆች የንጉሡ ቀራቢዎች ነበሩ። 3ከኤዶትም የኤዶትም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ሱሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መታትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ከአባታቸው ከኤዶትም ጋር በበገና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር። 4ከኤማን የኤማን ልጆች፤ ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዓዛርዔል፥ ሱባኤል፥ ኢየሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጌዶላቲ፥ ሮማንቴዔዜር፥ ዮስብቃሳ፥ ሜኤላቴ፥ ሆቴር፥ መሐዝዮት፤ 5እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ ያደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ቃል በንጉሡ ፊት የሚዘምረው#ዕብ. “የንጉሡ ባለ ራእይ የሆነው” ይላል። የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው። 6እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና፥ በመሰንቆም ከአባታቸው ጋራ የእግዚአብሔርን ቤት ለማገልገል ወደ ንጉሡ ቀርበው ያመሰግኑ ነበር። አሳፍም ኤዶትምም ኤማንም ያመሰግኑ ነበር። 7የብልሃተኞቹም ቍጥር እግዚአብሔርን ለማመስገን ከሚያውቁ ከወንድሞቻቸው ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ። 8ሁሉም ተካክለው፥ ታናሹም ታላቁም፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ እነርሱም ፍጹማንና የተማሩ ነበሩ።
9የመጀመሪያው ዕጣ ለአሳፍ ወገን ለዮሴፍ ለወንድሞቹና ለልጆቹ ለዐሥራ ሁለቱ ደረሳቸው፤ ሁለተኛውም ዕጣ ለጎዶልያስ ለልጆቹና ለወንድሞቹ ለዐሥራ ሁለቱ ደረሳቸው፤ 10ሦስተኛው ለዘኩር ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 11አራተኛው ለይጽሪ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 12አምስተኛው ለናታንያስ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ። 13ስድስተኛው ለቡቅያ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 14ሰባተኛው ለይስርኤል ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 15ስምንተኛው ለኢያስያ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 16ዘጠነኛው ለማታንያስ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 17ዐሥረኛው ለሰሜኢ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 18ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 19ዐሥራ ሁለተኛው ለኢሰብያ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 20ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 21ዐሥራ አራተኛው ለማታትያስ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 22ዐሥራ አምስተኛው ለኢየሪሙት ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 23ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 24ዐሥራ ሰባተኛው ለዮስባቃጥ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 25ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 26ዐሥራ ዘጠነኛው ለማኤላቲ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 27ሃያኛው ለኤልያታ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 28ሃያ አንደኛው ለኦትሪ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 29ሃያ ሁለተኛው ለጌዶላቲ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 30ሃያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 31ሃያ አራተኛው ለሮማንቴዔዜር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ ወጣ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 25: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ