መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 24
24
የካህናት አገልግሎት ድርሻ
1የአሮንም ልጆች ሰሞን ይህ ነው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ። 2ናዳብና አብዩድ ግን ልጆች ሳይወልዱ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ የአሮን ልጆች አልዓዛርና ኢታምርም ካህናት ሆነው አገለገሉ። 3ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ሳዶቅን፥ ከኢታምርም ልጆች አቤሜሌክን እንደ ቍጥራቸው፥ እንደ አገልግሎታቸውና እንደ እየአባቶቻቸው ቤቶች ከፍሎ መደባቸው። 4የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ዐሥራ ስድስት አለቆች፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ። 5ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የንዋያተ ቅዱሳቱና የእግዚአብሔር ቤት አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ። 6ከሌዋውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሓፊው ሳምያስ በንጉሡና በአለቆቹ ፊት ፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቤሜሌክ ፊት ፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ጻፈ።
7መጀመሪያውም ዕጣ ለኢያሬብ ወጣ፤ ሁለተኛውም ለኢያድያ፥ 8ሦስተኛውም ለካሬም፥ አራተኛውም ለሴዓሪን፥ 9አምስተኛውም ለመልክያ፥ ስድስተኛውም ለሜዒያኢም፥ 10ሰባተኛውም ለአቆስ፥ ስምንተኛው ለአብያ፥ 11ዘጠነኛው ለኢያሱ፥ ዐሥረኛው ለሴኬንያ፥ 12ዐሥራ አንደኛው ለኤልያሴብ፥ ዐሥራ ሁለተኛው ለኤልያቄም፥ 13ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፋዕ፥ ዐሥራ አራተኛው ለኤሳባእ፥ 14ዐሥራ አምስተኛው ለቤልጋዕ፥ ዐሥራ ስድስተኛው ለኤሜር፥ 15ዐሥራ ሰባተኛው ለኢያዜር፥ ዐሥራ ስምንተኛው ለአፌስ፥ 16ዐሥራ ዘጠነኛው ለፈታሕያ፥ ሃያኛው ለሕዝቄል፥ 17ሃያ አንደኛው ለአኬኖ፥ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙሄል፥ 18ሃያ ሦስተኛው ለደላኢያ፥ ሃያ አራተኛው ለሙዓዚ። 19የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ በአባታቸው በአሮን እጅ እንደ ተሰጣቸው ሥርዐት ወደ እግዚአብሔር ቤት ይገቡ ዘንድ እንደ እየአገልግሎታቸው ቍጥራቸው ይህ ነበረ።
የሌዋውያን የስም ዝርዝር
20ከቀሩትም የሌዊ ልጆች፤ ከእንበረም ልጆች ስባሄል፤ ከስባሄል ልጆች ኢያዳእያ፤ 21ከአረብያም ልጆች የአረብያ ልጅ አራድያ፥ አለቃው ኢያስያስ፤ 22ከኢስዓራውያን ሰሎሞት፤ ከሰሎሞት ልጆች ኤናት፤ 23ከኢዩዲዩ#ዕብ. “ከኬብሮንም” ይላል። ልጆች አለቃው ይሪያ፥ #“አለቃው ይሪያ” የሚለው በግሪክ እና በግእዝ የለም። ሁለተኛው አማርያ፥ ሦስተኛው ኢያዚሄል፥ አራተኛው ኢያቁምያ፤ 24የኢያዝሄል ልጅ ሚካ፤ የሚካ ልጅ ሳሜር፤ 25የሚካ ወንድም ኢሳእያ፤ የኢሳእያ ልጅ ዘካርያስ፤ 26የሜራሪ ልጆች ሞዓሊና ሐሙሲ፤ የዖዝያስ ልጅ ባኒ፤ 27የሜራሪ ልጆች፤ ከዖዝያ ይሰዓም፥ ዝኩር፥ አብዲ፤ 28የሞዓሊ ልጅ አልዓዛር፥ እርሱም ልጆች አልነበሩትም፤ 29ከቂስ፤ የቂስ ልጅ አራሜሄል፤ 30የሐሙሲ ልጆች፤ ሞዓሊ፥ ኤዳር፥ ኢያሪሞት። እነዚህ እንደ አባቶቻቸው ቤቶች የሌዋውያን ልጆች ነበሩ። 31እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላላቆች እንደ ታናናሽ ወንድሞቻቸው፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 24: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ