መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 17
17
ነቢዩ ናታን ለንጉሥ ዳዊት የነገረው ቃል
(2ሳሙ. 7፥1-17)
1እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩ ናታንን፥ “እነሆ፥ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ግን በመጋረጃዎች ውስጥ ተቀምጣለች” አለው። 2ናታንም ዳዊትን፥ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና በልብህ ያለውን ሁሉ አድርግ” አለው። 3በዚያም ሌሊት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጣ፤ እንዲህም አለው፦ 4“ሂድ፥ ለአገልጋዬ ለዳዊት ንገረው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጡ እኖርበት ዘንድ ቤትን የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም፤ 5ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳንና በማደሪያ ኖርሁ እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁም።#ዕብ. “ከድንኳን ወደ ድንኳን ከማደሪያ ወደ ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ” ይላል። 6ከእስራኤል ሁሉ ጋር ባለፍሁበት ስፍራ ሁሉ፥ ስለ ምን ቤትን ከዝግባ እንጨት አልሠራችሁልኝም? ብዬ ሕዝቤን ይጠብቅ ዘንድ ከእስራኤል ፈራጆች ላዘዝሁት ለአንዱ በውኑ ተናግሬአለሁን? 7አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ መንጋውን ስትከተል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ መርጬ#“መርጬ” የሚለው በዕብ. እና በግሪክ የለም። ወሰድሁህ። 8በሄድህበትም ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ፤ በምድርም ላይ እንዳሉ እንደ ታላላቆች ስም ለአንተ ስምን አደረግሁ። 9ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርግለታለሁ፥ በዚያም እተክለዋለሁ፥ በስፍራውም ይቀመጣል፤ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ የኀጢአትም ልጆች እንደ ቀድሞው አያስጨንቁትም፤ 10በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ፈራጆችን ካስነሣሁበት ጊዜ ጀምሮ ጠላቶችህን ሁሉ አዋርዳቸዋለሁ፤ አንተንም ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ። እግዚአብሔር ደግሞ ቤትን ይሠራልሃል። 11ወደ አባቶችህም ትሄድ ዘንድ ዕድሜህ በተፈጸመ ጊዜ ከአብራክህ የተወለደ ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ። 12እርሱ ቤትን ይሠራልኛል ፤ ዙፋኑንም ለዘለዓለም አጸናለሁ። 13እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆነኛል፤ ከአንተ አስቀድሞ ከነበሩት እንዳራቅሁ፥ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም። 14ለቤቴም ታማኝ አደርገዋለሁ መንግሥቱም ለዘለዓለም ነው፤#ግሪክኛው “በቤቴና በመንግሥቴም አጸናዋለሁ” ይላል። ዙፋኑም ለዘለዓለም ይጸናል።” 15እንደዚህ ነገር ሁሉ እንደዚህም ራእይ ሁሉ ነቢዩ ናታን ለዳዊት ነገረው።
የዳዊት የምስጋና ጸሎት
(2ሳሙ. 7፥18-29)
16ንጉሡም ዳዊት ገባ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፥ “አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ለዘለዓም የወደድኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው? 17አምላክ ሆይ፥ ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፤ ስለ አገልጋይህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው#ግሪኩ “ሰው ባልንጀራውን እንደሚያይ ተመለከትኸኝ” ይላል። ተመለከትኸኝ። አቤቱ፥ አምላክ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ። 18አንተ ባሪያህን ታውቀዋለህና ለባሪያህ ስለ ተደረገው ክብር ዳዊት ጨምሮ የሚለው ምንድን ነው? 19እንደ ልብህም ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ ለእኔ አደረግህ። 20አቤቱ፥ እንዳንተ ያለ የለም፤ በጆሮአችንም እንደ ሰማን ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም። 21አንተ እግዚአብሔር ከግብፅ ካወጣኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብን በማሳደድ ታላቅና የከበረ ስምን ለአንተ ታደርግ ዘንድ፥ ለአንተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደ መራኸው እንደ አንተ ሕዝብ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ የለም። 22ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘለዓለም ሕዝብህ አደረግኸው፤ አንተም አቤቱ፥ አምላክ ሆንሃቸው። 23አሁንም፥ አቤቱ፥ ስለ ባሪያህና ስለ ቤቱ የተናገርኸው ቃል ለዘለዓለም የታመነ ይሁን፤ እንደ ተናገርህም አድርግ። 24ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እርሱ የእስራኤል አምላክ ነው፤ በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው ይባል ዘንድ ስምህ ለዘለዓለም ጽኑና ታላቅ ይሁን፤ የአገልጋይህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሁን። 25አምላኬ ሆይ፥ ቤት እንድትሠራለት ለባሪያህ በጆሮው ገልጠሃልና ስለዚህ አገልጋይህ ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ ባለሟልነትን አገኘ። 26አሁንም፥ አቤቱ፥ አንተ አምላክ ነህ፤ ይህንም መልካም ነገር ለባሪያህ ተናግረሃል። 27አሁንም በፊትህ ለዘለዓለም ይኖር ዘንድ የአገልጋይህን ቤት ትባርክ ዘንድ ጀምረሃል፤ አንተም አቤቱ፥ ባርከኸዋል፤ ለዘለዓለምም ቡሩክ ይሆናል።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 17: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ