መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 14
14
ዳዊት በኢየሩሳሌም የፈጸማቸው ተግባራት
(2ሳሙ. 5፥11-16)
1የጢሮስም ንጉሥ ኪራም ቤት ይሠሩለት ዘንድ መልእክተኞችን፥ የዝግባ እንጨትንም፥ ጠራቢዎችንም፥ አናጢዎችንም ወደ ዳዊት ላከ። 2ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል፥ መንግሥቱ እጅግ ከፍ ብሎአልና እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን እንዳዘጋጀው ዳዊት ዐወቀ።
3ዳዊትም በኢየሩሳሌም ሌሎች ሚስቶችን ጨምሮ አገባ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት። 4በኢየሩሳሌምም የተወለዱለት የልጆቹ ስም ይህ ነው፤ ሳማ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፤ 5በዓር፥ ኤሊሳዒ፥ ኤሌፋላት፤ 6ናጌት፥ ናፋት፥ ያፍያ፥ 7ኤሊሳማ፥ በለዓዳ፥ ኤሊፋላት።
ዳዊት በፍልስጥኤማውያን ላይ የተቀዳጀው ድል
(2ሳሙ. 5፥17-25)
8ፍልስጥኤማውያንም ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ዳዊትን ሊፈልጉ ወጡ፤ ዳዊትም በሰማ ጊዜ ሊጋጠማቸው ወጣ። 9ፍልስጥኤማውያንም መጥተው በኀያላን ሸለቆ ተሰበሰቡ። 10ዳዊትም፥ “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ” አለው። 11ዳዊትም ወደ በኣልፐራሲን ወጣ፤ በዚያም ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታቸው። ዳዊትም፥ “ውኃ እንዲያጠፋ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አጠፋቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣልፐራሲን ብለው ጠሩት። 12አማልክቶቻቸውንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊትም፥ “በእሳት አቃጥሉአቸው” ብሎ አዘዘ።
13ፍልስጥኤማውያንም ደግሞ በኀያላን ሸለቆ ተሰበሰቡ። 14ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “አትውጣ፥ በኋላቸውም አትከተላቸው፤ ነገር ግን ከኋላቸው ዙረህ ቅረባቸው።#ዕብ. “ከእነርሱ ዙረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ ወደ እነርሱ አትውጣ” ይላል። 15በሾላውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽውሽውታ ድምፅ ስትሰማ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ሊመታ እግዚአብሔር በፊትህ ይወጣልና በዚያን ጊዜ ወደ ሰልፍ ውጣ” አለው። 16ዳዊትም አምላኩ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ከገባዖንም ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መታ። 17የዳዊትም ዝና በየሀገሩ ሁሉ ወጣ፤ መፈራቱንም እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ አደረገ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 14: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ