መጽሐፈ ጥበብ 10

10
ጥበብና ታሪክ
ከአዳም እስከ ሙሴ
1 # ዘፍ. 1፥26-28። የመጀመሪያውን ሰው፥ የዓለምን አባት፥
በመልካም ሁኔታ ይቀረጽ ዘንድ፥
ከወደቀበት ያዳነችው እርሷ ናት፤
2ሁሉን ይገዛም ዘንድ ኃየልን ሰጠችው።
3 # ዘፍ. 4፥8-13። ክፉው ሰው በተቆጣ ጊዜ ግን እርሷን ተዋት፤
በንዴት ወንደሙን በመግደሉ በጥፋት ላይ ወደቀ።
4 # ዘፍ. 7፥1—8፥22። በእርሱ ጥፋት መሬት በውሃ በተጥለቀለቀች ጊዜ፥
አሁንም ያዳነችው ጥበብ ናት።
ጻድቁን ሰው በእንጨት አንሳፋ አዳነችው።
5 # ዘፍ. 11፥1-9፤ 12፥1-3፤ 22፥1-19። ሰዎች ክፉ በመፈጸም ሲያድሙ፥ እንዲበጣበጡ ተፈረደባቸው፤
ያንጊዜ ጻድቁን ሰው ለየች፤ በእግዚአብሔርም ፊት አቀረበች፤
ከልጁም ኀዘን አበረታችው።
6 # ዘፍ. 19፥1-29። ክፉዎች በጠፉ ጊዜ ጻድቁን ያዳነች እርሷ ናት፤
ስለ ክፋታቸው ምስክር ይሆን ዘንድ፥ ከነደደው መሬት፥
7ተክሎች የማይበስል ፍሬ ከተሸከሙበት፥
ላላመነች ነፍስ የቆመው መታሰቢያ የጨው ዓምድ ሆኖ ከቀረበት፥
በአምስቱ ከተሞች ላይ ከወረደው እሳት ሸሽቶ እንዲያመልጥ ረድታዋለች።
8የጥበብን መንገድ ባለመሻት፥ ጥሩውን ለማወቅ ካለመቻላቸው በላይ
የስሕተታቸውን መታሰቢያ ጥለው አልፈዋል፤
በዚህም ገበናቸውን ሁሉም ያየዋል።
9ጥበብ ግን አገልጋዮቿን ሁሉ፥ ከመከራ ታደገቻቸው።
10 # ዘፍ. 27፥43፤ 28፥10-22፤ 32፥24-30። ከወንድሙ ቁጣ የሚሸሸውን ጻድቅ ሰው፥
በቀና መንገዶች መራችው፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት አሳየችው፤
ስለ ቅዱስ ነገሮችም ያውቅ ዘንድ አስተማረችው፤
ድካሙ ፍሬ እንዲያፈራ አደረገች፤ የጥረቱንም ዋጋ ሰጠችው።
11ከጨቋኞችና ከስግብግቦች ጋር ስፋለም፥ ከጐኑ ቆመች፤
ባለጸጋም አደረገችው።
12ከጠላቶቹ ጠበቀችው፤ ካጠመዱበትም ወጥመድ አወጣችው።
በመራራዉ የትግል ወቅት ሸለመችው።
የተቀደሰ ተግባር ከሁሉም በላይ መሆኑን አስተማረችው።
13 # ዘፍ. 37፥12-36፤ 39፥1-23፤ 41፥37-44። በተሸጠ ጊዜ ከጻድቁ ሰው አልራቀችም፤
ከኃጢአትም መንጥቃ አወጣችው።
14ከጉድጓድ ውስጥ አብራው ገባች፤
በሰንሰለት በታሰረ ጊዜ አልተወችውም፤
በትረ መንግሥቱን እስኪጨብጥ፥ በጨቋኞችም ላይ ሥልጣንን እስኪያገኝ፥ ከጐኑ አልጠፋችም።
በውሸት ያሙትን ሁሉ፥ ሐሰተኞች እንደ ሆኑ አግልጣለች፤
ዘላለማዊ ክብርንም አጐናጽፋዋለች።
ወደ ተስፋይቱ ሀገር መመለስ
15 # ዘፀ. 1፥1—15፥21። ንጹሕ ዘር የሆነውን የቀደሰ ሕዝብ፥
ከጨቋኞች መዳፍ የታደገችው ጥበብ ነች።
16በጌታ አገልጋይ ነፍስ ውስጥ ዘልቃ፥
በታምራትና በምልክቶች አስፈሪ ነገሥታትን የተቋቋመች ጥበብ ናት።
17ለተቀደሱ ሰዎች የልፋታቸውን ዋጋ ከፍላለች፤
በአስደናቂ መንገድም መራቻቸው፤ በቀን ተገን፤
በሌሊት የኮከብ ብርሃን ሆነችላቸው።
18ቀይ ባሕርን አሻገረቻቸው፤ በግዙፍ የውሃ አካልም ውስጥ መራቻቸው፤
19ጠላቶቻቸውን ግን አስመጠች፤ ኋላም ከጥልቁ ጉድጓድ ተፋቻቸው።
20ስለዚህ ጻድቃን ክፉዎቹን በረበሯቸው፤
ጌታ ሆይ የተቀደሰውን ስምህንም አመስግኑ፤
በአንድነት ጠባቂ ክንድህን አወድሱ፤
21ጥበብ የዱዳዎችን አንደበት ከፍታለች፤
የሕፃናትንም ምላስ ፈትታለችና።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ