መጽ​ሐፈ ጦቢት 13

13
ጽዮን
1ጦቢትም እንዲህ አለ፦ “ለዘለዓለም የሚኖር እግዚአብሔር ይባረክ፥ መንግሥቱ በዘመናት ሁሉ ይኖራልና። 2የሚቀጣም፥ የሚምርም እርሱ ነውና። እርሱ ወደ ሲኦል ጥልቀት ያወርዳል፥ ከጥልቅ ጥፋትም ያወጣል፥ ከእጁ የሚያመልጥ ማንም የለም፤ 3የእስራኤል ልጆች ሆይ በመንግሥታት መካከል ምስጋናውን አውጁ፥ በመካከላቸው በትኖአችኋልና፤ 4#ኢሳ. 63፥16፤ ኤር. 3፥4፤ ጥበ. 14፥3፤ ሲራ. 23፥1፤4፤ ማቴ. 6፥9።እዚያም ትልቅነቱን አሳይቷችኋል፥ በሕያዋን ሁሉ ፊት አሞግሱት፤ እርሱ ጌታችን ነው፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ እርሱ አባታችን ነው፥ እርሱ ለዘለዓለም አምላክ ነው። 5በኃጢአታችሁ ምክንያት ቢቀጣችሁም፥ በሁላችሁም ላይ ምሕረትን ያደርጋል፤ ተበታትናችሁ ከምትገኙባቸው አገሮች ሁሉ መካከል ይሰበስባችኋል። 6በፊቱ እውነትን የሆነውን ለማድረግ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ንፍሳችሁ ወደ እርሱ ከተመለሳችሁ፥ እርሱም ወደ እናንተ ይመለሳል፥ ፊቱንም ከዚህ በኋላ አይሰውርም። ያደረገላችሁን አስቡ፥ ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ ምስጋናን ስጡት፤ የጽድቅ ጌታ ባርኩት፤ የዘመናትንም ንጉሥ አሞግሱት። እኔ ተማርኬ በመጣሁበት አገር ሆኜ፥ ምስጋናውን እዘምራለሁ፤ ኃጢአት በሠራች ከተማ ላይ ኃይሉንና ትልቅነቱን አስታውቃለሁ። ኃጢአተኞች ወደ እርሱ ተመለሱ፥ ስራችሁ በፊቱ ትክክለኛ ይሁን፥ ምናልባት ምሕረት ያደርግላችሁ፥ ይራራላችሁ ይሆናል።” 7እኔ አምላኬን አሞግሰዋለሁ፥ ነፍሴም በሰማዩ ንጉሥ ትደሰታለች። 8ትልቅነቱ በሁሉም በምላስ ላይ ይሁን፤ ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይዘምር። 9#ኢሳ. 60፥1-22፤ ራእ. 21፥9—22፥5።ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በሠራሽው ሥራ ምክንያት እግዚአብሔር ይቀጣሻል፤ ነገር ግን ለጻድቅ ልጆች አሁንም ይራራላቸዋል። 10ቤተ መቅደሱ በውስጥሽ በደስታ እንዲሠራ፥ ለጌታ የሚገባውን ምስጋና አቅርቢለት፥ የዘመናትንም ንጉሥ ባርኪ፤ በውስጥሽ ያሉትን ስደተኞች እንዲያጽናና፥ በአንቺ ውስጥ ያሉ ያዘኑትን ሁሉ በመጭው ትውልድ ዘመን ሁሉ እንዲያፈቅራቸው። 11በምድር ሁሉ ላይ ደማቅ ብርሃን ያበራል፥ ለሰማዩ ንጉሥ በእጆቻቸው ሥጦታ ይዘው፥ ከሁሉም የምድር ዳርቻዎች፥ ብዙ መንግሥታት ከሩቅ ወደተቀደሰው ስምህ ይመጣሉ፥ ከትውልድ ወደ ትውልድ ደስታቸውን ያውጃሉ፥ የተመረጠችውም ስም ለመጪው ትውልድ ይኖራል። 12የሚያዋርዱሽ ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ፥ የሚያጠፉሽ ሁሉ፥ ግንቦችሽን የሚያፈርሱ ሁሉ፥ ህንፃዎችሽን የሚያወድሙ፥ ቤቶችሽን የሚያቃጥሉ ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ። መልሶ የሚገነባሽ ግን ለዘለዓለም የተባረኩ ይሁኑ። 13በዚያን ጊዜ በጻድቁ ልጆች ምክንያት ትፈነድቂያለሽ፥ ትደሰቻለሽም፤ እነርሱ ሁሉ ተሰብስበው የዘመናትን ጌታ ይባርካሉና። 14አንቺን የሚወዱ ሁሉ የተባረኩ ናቸው፥ በሰላምሽ የሚደሰቱ የተባረኩ ናቸው፥ በደረሰብሽ ቅጣት ሁሉ ስለ አንቺ የሚያዘኑ የተባረኩ ናቸው፤ እነርሱ በመጪዎቹ ቀኖች መባረክሽን አይተው በውስጥሽ ሆነው ይደሰታሉና። 15ነፍሴ ሆይ ታላቁን ንጉሥ፥ ጌታን ባርኪ፤ 16ምክንያቱም ኢየሩሳሌም ለዘለዓለም ቤቱ ሆና እንደ አዲስ ትታነጻለችና፥ የአንቺን ክብር ለማየትና፥ የሰማዩን ንጉሥ ለማመሰገን፥ ከቤተሰቦቼ አንዱ እንኳ ቢቀር፥ ምንኛ ደስታ ነበር፤ የኢየሩሳሌም በሮች ከሰንፔርና ከኤመራልድ ይሠራሉ፥ ግንቦችሽም ከውድ ዐለቶች ይፈለፈላሉ፥ የኢየሩሳሌም ህንፃዎች ከወርቅ፥ ቅጥሮቻቸውም ከንጹህ ወርቅ ይሠራሉ፤ 17የኢየሩሳሌም መንገዶች በቀያይ የከበሩ ድንጋዮችና በዖፌር ድንጋዮች ይሸፈናሉ። 18የኢየሩሳሌም በሮች የምስጋና መዝሙርን ያስተጋባሉ፥ ቤቶችም በሙሉ “ሃሌ ሉያ! የእስራኤል አምላክ ይባረክ” ይላሉ። በውስጥሽም ቅዱሱን ስም፥ ለዘለዓለም ዓለም ይባርካሉ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ