መጽሐፈ ሲራክ 50
50
ሊቀ ካህኑ ስምዖን
1በሕይወት ዘመኑ ቤተ መቅደሱን ያደሰ፥ የእግዚአብሔርን ቤት የገነባ፥ የኦንያስ ልጅ ሊቀ ካህናት ስምዖን ነበር። 2መሠረቱን በእጥፍ ጥልቀት ገነባ፥ በቤተ መቅደሱ አጠገብ የሚገኙትን ከፍተኛ መደገፊያዎች ሠራ። 3ኩሬው የተቆፈረው በእርሱ ጊዜ ነው፥ እርሱም እንደ ባሕር የገዘፈ የውሃ ማጠራቀሚያ ነው። 4ሕዝቡን ከጥፋት ለማዳን በማሰቡ፥ ከተማዋንም ከከበባ ለመከላከል ምሽግ ሠራ 5መገረጃውን ገልጦ ብቅ ሲልና በሕዝቡ ተከቦ ሲራመድ፥ እንደምን ያስደስት ነበር! 6በደመና መካከል እንደምትወጣው የንጋት ኮከብ፥ እንደ ሙሉ ጨረቃ፥ 7በልዑል እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደምታበራው ፀሐይ፥ 8እንደ ፀደይ ወራት ጽጌረዳ፥ በውሃ ዳር እንደበቀለች ነጭ አበባ፥ በበጋ እንደሚታየው የዕጣን ዛፍ ቅርንጫፍ፥ 9በጥናው ላይ እንዳለው እሳትና ዕጣን፥ በከበረ ደንጊያ እንደተለበጠ ግዙፍ የወርቅ ሳህን፥ 10ፍሬው እንደከበደው የወይራ ዛፍ፥ ደመናዎችን ለመንካት እንደሚምዘገዘግ የጥድ ዛፍ፥ የደስ ደስ ነበረው። 11የክብር ቀሚሱን ሲለብስና ጌጣጌጦቹን ሲያደርግ፥ ወደተቀደሰው የመሠዊያ ሲወጣና አካባቢውን ግርማ ሞገሱ ሲያደምቀው፥ 12ከመሠዊያው ምድጃ አጠገብ ቆሞ፥ ከካህናቱ እጅ ድርሻዎቹን ሲቀበል፥ የሊባኖስ ዝግባ በቅጠሉ እንደሚሸፈን፥ በዘንባባ ግንዶች እንደተከበበ ሁሉ፥ እርሱንም ወንድሞቹ ከበውት አክሊል ይሆኑታል። 13የአሮን ልጆች ሁሉ፥ በክብር አጊጠው፥ ለጌታ የሚቀርበውን መሥዋዕት፥ በእጆቻቸው እንደ ያዙ በመላው እስራኤል ጉባኤ ፊት ይቀርባሉ። 14እርሱም በበኩሉ በመሠዊያው ሥርዓተ አምልኮን ይፈጽማል፤ ለኃያሉና ለታላቁ አምላክ መሥዋዕቶቹን በክብር ያቀርባል። 15ጽዋውን ያነሣል፥ የወይኑንም ጭማቂ በዙሪያው ያፈሳል፥ በመሠዊያው ግርጌ ይረጫል፤ መዓዛውም የዓለምን ንጉሥ ልዑል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል። 16ያኔ የአሮን ልጆች ይጮሃሉ፥ የብረት ጡሩምባቸውን ይነፋሉ፤ በእግዚአብሔር ፊት አስታዋሽ የሚሆን ከፍተኛ ድምፅ ይሰማል። 17ሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት በፊታቸው መሬት ላይ ይደፋሉ፤ ለጌታቸው ለኃያሉ ልዑል እግዚአብሔር ያላቸውንም ፍቅር ይገልጻሉ፤ 18መዘምራኑም የምስጋና መዝሙር ያሰማሉ፥ የሁሉም ድምፅ ዜማው ጣፋጭ ነው። 19የጌታ ሥርዓተ ጸሎትና ሥርዓተ አምልኮው እስኪፈጸም ድረስ፥ በመሐሪው አምላክ ፊት ይጸለያሉ፥ ታላቁን አምላክ ይማፀናሉ፤ 20#ዘኍ. 6፥24-27።እርሱም ወደ ታች ወርዶ፥ በመላው እሥራኤል ጉባኤ ላይ እጆቹን ያነሣል፥ ስሙን ለመጥራት ታድሏልና የጌታ ቡራኬም በአንደበቱ ይናገራል። 21ሕዝቡም የልዑል እግዚአብሔርን በረከት ለመቀበል በሁለተኛ ጊዜ ይሰግዳሉ።
ልመና
22በየትኛውም ቦታ፥ የታላላቅ ሥራዎችን ፈጣሪ፥ ከእናታችን ማሕፀን ጀምሮ ሕይወታችንን የታደገውን፥ በምሕረቱም የሚጠብቀንን፥ የሁሉንም አምላክ አመስግኑ። 23ደስተኛ ልብ ይስጠን፤ በዘመናችን ደስታ፥ ለእስራኤል ደግሞ ዘላለማዊ ሰላምን ይስጥ። 24ምሕረቱ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ይሁን፥ በዘመናችን ደኀንነትን ይስጠን።
አኃዛዊ ምሳሌ
25ነፍሴ የምትጠላቸው ሁለት ሕዝቦች አሉ፤ ሦስተኛው ፈጽሞ ሕዝብ አይደለም፥ 26የሴኤር ተራራ ሠፋሪዎች፥ ፍልስጥኤማውያንና በሴኬም የሚኖረው ማስተዋል የጐደለው ሕዝብ ነው።
መደምደሚያ
27በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የቀረበው፥ የዕውቀትና የጥበብ ትምህርት ነው። 28ይህ ከልብ የመነጨ የጥበብ ዝናብ የፈሰሰው፥ ከኢየሩሳሌም ሲራክ አልዓዛር ልጅ ከኢየሱስ ነው። በልቡ የሚያሳድራቸውም ሰው ጥበበኛ ይሆናል። 29በሥራ የሚያውላቸው ደግሞ በምንም አይረታም፤ መንገዱ የጌታ ብርሃን ነውና።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 50: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ