መጽሐፈ ሲራክ 44
44
ለ. በታሪክ ውስጥ ለቀድሞ አባቶች የቀረበ ውዳሴ
1ታላቅ ሰዎችን፥ አባቶቻችንን፥ እንደ ትውልዳቸው ቅደም ተከተል እናመስግናቸው። 2ጌታ ክብርን በብዛት ፈጥሯል፤ ታላቅነቱንም ከጥንት ጀምሮ አሳይቷል። 3አንዳንዶች ነገሥታት ሆኑ፥ በኃያልነታቸውም ገናኖች ነበሩ፥ ሌሎች ብልህ አማካሪዎች፥ ትንቢትም ተናጋሪዎች ነበሩ። 4ሕዝቡን በምክሮቻቸው ይመሩ፥ የሕዝብን ፍላጐት የተረዱ፥ ጥበብን ያስተማሩ ነበሩ። 5የሙዚቃ ስለቶችን የነደፉ፤ የውዳሴ ቅኔዎችንም የጻፉ ነበሩ። 6ሃብታሞችና ኃያላንም ሆነው በሰላም በቤታቸው የሚኖሩ ነበሩ። 7እኒህ ሁሉ በጊዜው በነበሩ ሰዎች ዘንድ፤ የተከበሩ የዘመናቸውም ፈርጥ ነበሩ። 8አንዳንዶች ስማቸውን ትተው አልፈዋል፥ ውሳሴዎቻቸውም እስከ ዛሬ ይዘምራሉ። 9ቀሪዎች ግን እንዳልተፈጠሩ ሁሉ ያለመታሰቢያ ቀርተዋል፥ እንዳልነበሩም ሆነዋል፤ ከእነርሱም በኋላ ልጆቻቸው እንዲሁ ይሆናሉ። 10ነገር ግን መልካም ተግባሮቻቸው ያልተዘነጉ ታላላቅ ሰዎችም አሉ። 11በዘራቸም መልካም ውርስ፥ የሆኑትን ልጆቻቸውን ያገኛሉ። 12ዘሮቻቸው ትእዛዛቱን ያከብራሉ፤ የልጅ ልጆቻቸውም የእነርሱን ፈለግ ይከተላሉ። 13ዘራቸው ለዘለዓለም ይኖራል፤ ዝናቸውም አይደበዝዝም። 14ሥጋቸው በሰላም ተቀብሯል፤ ስማቸው ግን በሁሉም ትውልዶች ዘንድ ይታወሳል፥ 15ሕዝቡ ስለ ጥበባቸው ያወሳል፥ በጉባኤውም ፊት ይመሰገናሉ።
ሄኖክ
16 #
ዘፍ. 5፥24፤ ዕብ. 11፥5፤ ይሁዳ 1፥14። ሄኖክ ጌታን በማስደሰቱ ወደ ገነት ገባ፤ ለትውልዶቹ ሁሉ መለወጥም ምሳሌ ሆነ።
ኖኀ
17 #
ዘፍ. 6፥9—9፥17። ኖኀ እውነተኛ ሰው ነበር፤ ቁጣም በወረደ ጊዜ ወራሽ ሆነ። የጥፋት ውሃ በወረደም ጊዜ በእርሱ የተነሣ ምድር ዘር ቀረላት። 18ከእርሱም ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳኖች ተደረጉ፤ እነርሱም ደግሞ ሕያዋን በጐርፍ እንደማይጠፉ አረጋገጡ።
አብርሃም
19 #
ዘፍ. 15፥1—17፥27፤ 22፥1-18። ታላቁ የሕዝቦች አባት አብርሃም በክብር የሚስተካከለው ከቶ አልነበረም። 20የልዑል እግዚአብሔርን ሕጐች ጠብቋል፤ ከእርሱም ጋር ቃል ገብቷል። ቃል ኪዳኑን በሥጋው አረጋገጠ፤ በመከራም ጊዜ ታማኝነቱን አስመሰከረ። 21እግዚአብሔርም በዘሩ አማካኝነት ሕዝቦችን ሊባርክ፥ እንደ ምድር ትቢያ ሊያበዛው፥ ዘሮቹን እንደ ከዋክብት ከፍ ከፍ ሊያደርግ፥ ምድርን ሊሰጣቸው፥ ከአንዱ ባሕር ወደ ሌላው፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻዎች ሊያወርሳቸው ማለለት። 22#ዘፍ. 17፥19፤ 26፥3-5፤ 27፥28፤ 28፥14።ሕዝቦችን እንደሚባርክ ለይስሐቅም አረጋግጦለታል። 23ቃል ኪዳኑን በያዕቆብ ራስ ላይ አሳረፈ፤ ቡራኬውን ሰጠው፤ ምድርን ርስቱ እንድትሆን ፈቀደ፤ እርሱም ሸነሸናት፤ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶችም አከፋፈላቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 44: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ