መጽሐፈ ሲራክ 42
42
1በሚከተሉት ሁናቴዎች ልታፍር አይገባህም፤ ሌሎች በሚያስቡትን በመፍራት፥ 2በልዑል እግዚአብሔር ሕግ ወይም በቃል ኪዳኑ፥ ከሐዲውን በነጻ በሚያሰናብት ፍርድ፥ 3ከመንገድ ጓደኛህ ጋር በመተሳሰብህ፥ ሀብትህን ወዳጆችህ በማካፈልህ፥ 4በሚዛኑና በክብደቱ ትክክለኛነት ጥቂት ወይም ብዙ በማትረፍህ፥ 5በንግድ ሥራ በመጠቀምህ፥ ልጆችህን በሚገባ በመቅጣትህ፥ አመፀኛውን አገልጋይ እስኪደማ በመግረፍህ፥ በኃጢአት አትውደቅ። 6ሚስትህ ሁሉን ማወቅ የምትሻ ከሆነ፥ ማሸጊያህን መጠቀም ያስፈልጋል፤ በርካታ እጆች ባሉበትም ንብረትህን ቆልፍ። 7ከዕቃ ቤት የሚወጣው ሁሉ በቁጥጥርና በሚዛን ይሁን፤ ወጪዎችና ገቢዎች ጽሑፍ ይመዝገቡ። 8አላዋቂውንና ሞኙን ሰው፥ ከወጣቶች ጋር የሚዳራውን ያረጀ ሽማግሌ፥ ለማረም አትፈር፤ በውል የተማርክ መሆንህን ያኔ ታሳያለህ፤ ሰውም ሁሉ ይህንኑ ያረጋግጥልሃል።
አባት ስለ ሴት ልጁ ያለበት ጭንቅ
9 #
ሲራ. 7፥24፤25፤ 26፥10-12። እርሷ ባታውቀውም፥ የሴት ልጅ አባት እንቅልፍ የለውም፤ ስለ እርሷ ሲያስብ እንቅልፉን ያጣል በወጣትነቷ ቆማ ብትቀር፥ ካገባች በኋላ ባሏ ቢጠላት፥ 10በልጃረገድነቷ ብትደፈር፥ ባባቷም ቤት ብትወልድ፥ ባል ኖሯት ብትማግጥ፥ ከጋብቻ በኋላ ብትመነኩስ በማለት ይጨነቃል። 11ልጅህ አስቸጋሪ ነችን? የጠላቶችህ መሳቂያ፥ የከተማው መዘባበቻ፥ የወሬኞች መጠቋቆሚያ እንዳታደርግህ፥ በሕዝብም ፊት ኀፍረትን እንዳታከናንብህ በብርቱ ጠብቃት።
ሴቶች
12ስለ ቁንጅናው ብላችሁ ወንድ አትመልከቱ፤ ከሴቶችም ጋር አትቀመጡ፥ 13ብል ከልብስ እንደሚመጣ፥ የሴት ክፋትም የሚመነጨው እንዲሁ ከሴት ነው። 14ከሴት ደግነት የወንድ ክፋት ይሻላል፤ ሴቶች ኀፍረትንና ጥላቻን ያመጣሉ።
የእግዚአብሔር ታላቅነት
ሀ. በተፈጥሮ ውስጥ
15የእግዚአብሔርን ሥራዎች ቀጥዬ አስታውሳችኋለሁ፤ ያየሁትንም እዘረዝራለሁ። በእግዚአብሔር ቃል ሥራዎች ሁሉ ሕያው ሆኑ፤ ፍጥረታትም ሁሉ ፈቃድን ይፈጽማሉ። 16የምታበራዋ ፀሐይ ሁሉንም ዘቅዝቃ ትመለከታለች፤ የእግዚአብሔርም ሥራ በክብሩ የተመላ ነው። 17እግዚአብሔር ድንቅ ሥራዎቹን ይገልጽ ዘንድ፤ ለቅዱሳኑ ሥልጣንን አልሰጠም፤ ኃያሉ እግዚአብሔር ሥራዎቹን ሁሉ አጽንቶ ፈጥሯል፤ ዓለምንም በክብሩ ፊት አቁሟል። 18ጥልቁን ጉድጓድ፥ የሰውንም ልብ ይመረምራል፤ አሳሳች መንገዶቻቸውንም ይመለከታል። ልዑል እግዚአብሔር ሁሉንም ያውቃል፤ የዘመናትንም ምልክቶች ያስተውለልና። 19ያለፈውንም፥ የሚመጣውንም ይናገራል፤ የሚሥጢራትንም አካሄድ ይገለጻል። 20አንዲት ሐሳብ አታመልጠውም፤ አንድም ቃል ከእርሱ አይሰወርም። 21በጥበብ የሠራቸውን ድንቅ ሥራዎች አስውቧቸዋል፤ መጀመሪያም መጨረሻም የለውም፥ ምንም አይቀነስበትም፥ ምንም አይጨመርበትም፥ እርሱ የማንንም ምክር አይሻም። 22የእጁ ሥራዎች ምንኛ ያስደስታሉ! ዓይንንስ ምንኛ ያጥበረብራሉ! 23ሁሉም ይኖራሉ፥ ዘላለማዊ ናቸው፤ በማንኛውም ሁኔታ ትእዛዙን ይፈጽማሉ። 24ሁሉም ጥንድና ተቃራኒ ናቸው፤ ጐደሎ አድርጐ የፈጠረው የለም። 25አንድ ነገር የሌላውን ከፍተኛ ችሎታ ያሟላል፤ ወደ ክብሩ አተኩሮ ተመልክቶስ ማን ታከተ?
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 42: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ