መጽሐፈ ሲራክ 28
28
1ተበቃዩን እግዚአብሔር ይበቀለዋል፤ እርሱ ኃጢአትን ይከታተላልና። 2#ማቴ. 6፥14፤ ማር. 11፥25።የጐረቤትህን በደል ይቅር ብትል፥ በጸለይህ ጊዜ ኃጢአትህ ይሠረይልሃል። 3አንዱ በሌላው ላይ ከተቆጣ፥ እንደምን ከጌታ ርኀራኄን ሊለምን ይችላል? 4ሰው ለመሰሉ ርኀራኄ ከሌለው፥ ኃጢአቱ ይሠረይለት ዘንድ መለመን ይቻለዋልን? 5ሥጋ ለባሽ ሆኖ እርሱ ካቄመ፤ ኃጢአቶቹን ማን ያስተሰርይለታል? 6የመጨረሻዎቹን ቅጣቶች አስታውስ፤ ሞትንና መበስበስን አስብ፤ የእግዚአብሔርንም ትእዛዞች ፈጽም። 7ትእዛዛቱን አስብ፤ በባልንጀራህ ላይ ክፉ አትመኝ፤ የልዑል እግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አስታውስ፤ የተፈጸመብህንም በደል እለፈው።
ፀብ
8ፀብን አሰወግድ፥ ኃጢአት አታብዛ፤ ቁጡ ሰው ፀብን ያባብሳልና። 9ኃጢአተኛ ሰው በወዳጆች መካከል ችግርን ይዘራል፤ ሰላም በሰፈነበት አለመግባባትን ይፈጥራል፤ 10እንደ ማገዶው ብዛት እሳቱ ይነዳል፤ የፀቡም ስፋት ከቁጣው መጠን ጋር ሲተያይ እንዲሁ ነው። የሰው ንዴቱ እንደ ጥንካሬው፥ የቁጣውም መጦፍ እንደ ሃብቱ ነው። 11ድንገተኛ ፀብ እሳት ይለኩሳል፤ ፈጣን ክርክር ደም ያፋስሳል። 12ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች፤ ብትተፋባት ትጠፋለች፤ ሁለቱም የአፍህ ውጤቶች ናቸው።
ምላስ
13 #
ሲራ. 51፥2-6፤ ያዕ. 3፥5-12። ተንኮለኛና አሾክሻኪ ሰው የተረገመ ይሁን፤ በሰላም የሚኖሩትን አበጣብጧልና። 14ሦስተኛዋም ምላስ የብዙዎችን ሰላም አናግታለች፤ ከሀገር ሀገርም እንዲሰደዱ ምክንያት ሆናለች፤ ከተሞችን አውድማለች፥ የታላላቶቹን ቤት አፍርሳለች። 15ሦስተኛዋ ምላስ ትክክለኛ ሚስቶችን አፋታለች፥ 16እርሷን የሚሰማ የአእምሮ ዕረፍት አይኖረውም፤ ሰላምም ከእርሱ ትርቃለች። 17ጅራፍ ሰንበር ያወጣል፤ ምላስ ግን አጥንት ይሰብራል። 18ብዙዎች ተሠይፈዋል፤ የበለጡ ደግሞ በምላስ ወድቀዋል። 19ከምላስ ያመለጠ፤ በቁጣዋ ያልተነካ፥ ቀንበሯን ያልተሸከመ፥ በሰንሰለቶቿም ያልተተበተበ የተባረከ ነው፤ 20ቀንበሯ የብረት፥ ሰንሰለቶቿም ከነሐስ ናቸውና። 21የምታመጣው ሞት አስከፊ ነው፤ ከእርሱ ሲኦል ይመረጣል። 22ጻድቃንን ማጥመድ አይቻላትም፤ በነበልባሏም አይነድዱም። 23ጌታን የሚርቁ ሁሉ ወደ እርሷ ይወድቃሉ፤ በመካከላቸውም ያለማቋረጥ ትነዳለች። እንደ አንበሳ ጉብ ትልባቸዋለች፤ እንደ ነብርም ትቦጫጭቃቸዋለች። 24ግቢህን በእሾህ አጥር እንድታጥር አትዘንጋ፤ ብርና ወርቅህንም ቆልፈህ አኑር፤ 25ለቃልህ ሚዛንና ልክ አብጅ፥ ለአፍህም በርና ቁልፍ ይኑርህ። 26ምላስህ እንዳታደናቅፍህ ተጠንቀቅ፤ ከወደቅህ አድፍጦ ለሚጠብቅህ ግዳይ ትሆናለህና።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 28: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ