የዮሐንስ ራእይ 14

14
በጉና መቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች
1 # ኢዩ. 3፥5፤ አብ. 17፤ የሐዋ. 2፥21፤ ሕዝ. 9፥4፤ ራእ. 7፥3። ከዚያም አየሁ፤ እነሆም በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ። 2ከሰማይም እንደ ብዙ ውሃ ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ የመሰለ ድምፅን ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምፅ ደርዳሪዎች በበገናቸው ሲደረድሩ እንደሚሰማው ዓይነት ድምፅ ነበር። 3#መዝ. 33፥3፤ 96፥1፤ 98፥1፤ ኢሳ. 42፥10።በዙፋኑም ፊት፥ በአራቱም ሕያዋን ፍጡራንና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያንን ቅኔ ማንም ሊማረው አልቻለም። 4እነዚህ ከሴቶች ጋር ያልረከሱ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበትም የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው። 5#ሶፎ. 3፥13።በአፋቸውም ውሸት አልተገኘም፤ ነውር የለባቸውም።
የሦስቱ መላእክት መልእክቶች
6በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ለማብሰር ዘላለማዊውን ወንጌል የያዘ ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤ 7በታላቅ ድምፅም “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውሃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት፤” አለ።
8 # ኢሳ. 21፥9፤ ኤር. 28፥8፤ ራእ. 18፥2። ሌላም ሁለተኛ መልአክ “አሕዛብን ሁሉ ከዝሙትዋ የቁጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው።
9ሌላም ሦስተኛ መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፤ “ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥ 10#ኢሳ. 51፥17፤ ዘፍ. 19፥24፤ ሕዝ. 38፥22።እርሱ ደግሞ በቁጣው ጽዋ ሳይቀላቅል#14፥10 ሳይቀጥን። ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር የቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል። 11#ኢሳ. 34፥10።የሥቃያቸውም ጢስ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ እንዲሁም የስሙን ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”
12የእግዚአብሔርን ትእዛዛትና የኢየሱስን እምነት የሚጠብቁት ቅዱሳን እዚህ ላይ ነው ጽናታቸው የሚፈለገው።
13ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ። “ይህንን ጻፍ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።” መንፈስም “አዎን! ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸው ይከተላቸዋልና፤” ይላል።
የምድር መከር ጊዜ
14 # ዳን. 7፥13። ከዚያም አየሁ፤ እነሆም ነጭ ደመና በደመናውም ላይ የሰው ልጅን#14፥14 መሢሕ፤ ዳን 7፥13ን ተመ.። የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው። 15#ኢዩ. 3፥13።ሌላም መልአክ ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው “የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፤ የምድሪቱ መከር ደርሶአልና፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። 16በደመናውም ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፤ ምድርም ታጨደች።
17ሌላም መልአክ በሰማይ ካለው መቅደስ ወጣ፤ እርሱም ደግሞ ስለታም ማጭድ ነበረው። 18በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን “ዘለላዎቹ በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቁረጥ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ተጣራ። 19መልአኩም ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፤ በምድርም ካለው ከወይን ዛፍ ቈርጦ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር የቁጣ ወይን መጥመቂያ ጣለ። 20#ኢሳ. 63፥3፤ ሰቆ.ኤ. 1፥15፤ ራእ. 19፥15።የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓም የሚደርስና እስከ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ድረስ የሚርቅ ደም ከመጥመቂያው ወጣ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ