መዝሙረ ዳዊት 6:1-7

መዝሙረ ዳዊት 6:1-7 መቅካእኤ

አቤቱ፥ በቁጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ። ዝያለሁና አቤቱ፥ ማረኝ፥ አጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ። ነፍሴም እጅግ ታወከች፥ አንተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው? አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥ ስለ ቸርነትህም አድነኝ። በሞት የሚያስታውስህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው? በመቃተቴ ደክሜአለሁ፥ ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን በእንባ አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።