መዝሙረ ዳዊት 145:13-16

መዝሙረ ዳዊት 145:13-16 መቅካእኤ

መንግሥትህ የዘለዓለም መንግሥት ናት፥ ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው። ጌታ በቃሎቹ የታመነ ነው፥ በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው፥ ጌታ የሚወድቁትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥ ያጎነበሱትንም ያነሣቸዋል። የሁሉ ዐይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፥ አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ። አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥ ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ።