መዝሙረ ዳዊት 144
144
1ስለ ጎልያድ፥ የዳዊት መዝሙር።
ጌታዬ ዐለቴ፥ ይባረክ፥
ለእጆቼ ሰልፍን፥ ለጣቶቼም ዘመቻን የሚያስተምር፥
2መሓሪዬና መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና መድኃኒቴ፥
ረዳቴና መታመኛዬም፥
ሕዝቤንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ።
3 #
ኢዮብ 7፥17። አቤቱ፥ እርሱን ታውቀው ዘንድ ሰው ምንድነው?
ታስብለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?
4 #
መዝ. 62፥10፤ 90፥9-10፤ ኢዮብ 7፥16፤ መክ. 6፥12፤ ጥበ. 2፥5። ሰው ከንቱን ነገር ይመስላል፥
ዘመኑ እንደ ጥላ ያልፋል።
5 #
ኢሳ. 63፥19። አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው ውረድም፥
ተራሮችን ዳስሳቸው ይጢሱም።
6መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው በትናቸውም፥
ፍላጾችህን ላካቸው አስደንግጣቸውም።
7-8እጅህን ከአርያም ላክ አድነኝም
ከብዙ ውኆች፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥
ቀኛቸው የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥
ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ።
9 #
መዝ. 33፥2-3። አቤቱ፥ አዲስ ቅኔ እቀኛልሃለሁ፥
ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።
10 #
መዝ. 18፥51። ለነገሥታት መድኃኒትን የሚሰጥ፥
ባርያውን ዳዊትን ከክፉ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው።
11አድነኝ፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥
ቀኛቸውም የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥
ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ።
12 #
መዝ. 128፥3። ልጆቻቸን በጉልማስነታቸው እንደ አዲስ አትክልት ይሁኑ፥
ሴቶች ልጆቻቸንም እንደ እልፍኝ ይመሩና ያጊጡ፥
13ዕቃ ቤቶቻቸንም ይሞሉ፥ በየዓይነቱም ዕቃ ይኑራቸው፥
በጎቻቸንም ብዙ ይውለዱ፥
በማሰማርያችንም ይብዙ፥
14 #
ኢሳ. 65፥19። ላሞቻቸንም የሰቡ ይሁኑ፥
ቅጥራቸውም መፍረሻና መውጫ አይኑረው፥
በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይኑር፥
15 #
መዝ. 33፥12። እንደዚህ የሚሆንለት ሕዝብ የተመሰገነ ነው፥
ጌታ አምላኩ የሆነለት ሕዝብ ምስጉን ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 144: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 144
144
1ስለ ጎልያድ፥ የዳዊት መዝሙር።
ጌታዬ ዐለቴ፥ ይባረክ፥
ለእጆቼ ሰልፍን፥ ለጣቶቼም ዘመቻን የሚያስተምር፥
2መሓሪዬና መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና መድኃኒቴ፥
ረዳቴና መታመኛዬም፥
ሕዝቤንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ።
3 #
ኢዮብ 7፥17። አቤቱ፥ እርሱን ታውቀው ዘንድ ሰው ምንድነው?
ታስብለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?
4 #
መዝ. 62፥10፤ 90፥9-10፤ ኢዮብ 7፥16፤ መክ. 6፥12፤ ጥበ. 2፥5። ሰው ከንቱን ነገር ይመስላል፥
ዘመኑ እንደ ጥላ ያልፋል።
5 #
ኢሳ. 63፥19። አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው ውረድም፥
ተራሮችን ዳስሳቸው ይጢሱም።
6መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው በትናቸውም፥
ፍላጾችህን ላካቸው አስደንግጣቸውም።
7-8እጅህን ከአርያም ላክ አድነኝም
ከብዙ ውኆች፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥
ቀኛቸው የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥
ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ።
9 #
መዝ. 33፥2-3። አቤቱ፥ አዲስ ቅኔ እቀኛልሃለሁ፥
ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።
10 #
መዝ. 18፥51። ለነገሥታት መድኃኒትን የሚሰጥ፥
ባርያውን ዳዊትን ከክፉ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው።
11አድነኝ፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥
ቀኛቸውም የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥
ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ።
12 #
መዝ. 128፥3። ልጆቻቸን በጉልማስነታቸው እንደ አዲስ አትክልት ይሁኑ፥
ሴቶች ልጆቻቸንም እንደ እልፍኝ ይመሩና ያጊጡ፥
13ዕቃ ቤቶቻቸንም ይሞሉ፥ በየዓይነቱም ዕቃ ይኑራቸው፥
በጎቻቸንም ብዙ ይውለዱ፥
በማሰማርያችንም ይብዙ፥
14 #
ኢሳ. 65፥19። ላሞቻቸንም የሰቡ ይሁኑ፥
ቅጥራቸውም መፍረሻና መውጫ አይኑረው፥
በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይኑር፥
15 #
መዝ. 33፥12። እንደዚህ የሚሆንለት ሕዝብ የተመሰገነ ነው፥
ጌታ አምላኩ የሆነለት ሕዝብ ምስጉን ነው።