መዝሙረ ዳዊት 132:11-14
መዝሙረ ዳዊት 132:11-14 መቅካእኤ
ጌታ ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትምም፥ እንዲህ ብሎ፦ ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ። ልጆችህ ኪዳኔን፥ ይህንም የማስተማራቸውን ኪዳኔን ቢጠብቁ፥ ልጆቻቸው ደግሞ በዙፋንህ ላይ ለዘለዓለም ይቀመጣሉ። ጌታ ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦ “ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፥ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።

