መዝሙረ ዳዊት 13
13
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 #
መዝ. 6፥4፤ 44፥25፤ 77፥8፤ 79፥5፤ 89፥47፤ 94፥3፤ ሰቆ.ኤ. 5፥20። አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ?
እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰውራለህ?
3እስከ መቼ በነፍሴ እጨነቃለሁ?
ትካዜስ እስከ መቼ ዕለቱን በሙሉ በልቤ ይሆናል?
እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይሸልላል?
4አቤቱ አምላኬ፥ እየኝ ስማኝም፥
ለሞትም እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ
5 #
መዝ. 38፥17። ጠላቴ፦ “አሸነፍሁት እንዳይል”፥
የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው።
6 #
መዝ. 116፥7። እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥
ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
ለረዳኝን ጌታ እዘምራለሁ፥
መልካምን አድርጎልኛልና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 13: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 13
13
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 #
መዝ. 6፥4፤ 44፥25፤ 77፥8፤ 79፥5፤ 89፥47፤ 94፥3፤ ሰቆ.ኤ. 5፥20። አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ?
እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰውራለህ?
3እስከ መቼ በነፍሴ እጨነቃለሁ?
ትካዜስ እስከ መቼ ዕለቱን በሙሉ በልቤ ይሆናል?
እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይሸልላል?
4አቤቱ አምላኬ፥ እየኝ ስማኝም፥
ለሞትም እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ
5 #
መዝ. 38፥17። ጠላቴ፦ “አሸነፍሁት እንዳይል”፥
የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው።
6 #
መዝ. 116፥7። እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥
ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
ለረዳኝን ጌታ እዘምራለሁ፥
መልካምን አድርጎልኛልና።