መጽሐፈ ነህምያ 13:1-2

መጽሐፈ ነህምያ 13:1-2 መቅካእኤ

በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ በሕዝቡ ጆሮ ከፍ ባለ ድምፅ አነበቡ፤ አሞናዊ ወይም ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ለዘለዓለም እንዳይገባ የሚል በዚያ ተጽፎ ተገኘ። ይህም ደግሞ የእስራኤልን ልጆች በምግብና በውኃ ስላልተቀበሉአቸውና እንዲረግማቸውም በለዓምን ስለ ገዙት ነው፤ ነገር ግን አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው።